ቀዳማዊት እመቤት ወ/ሮ ዝናሽ ታያቸው በግንባታ ላይ የሚገኘውን የቁስቋም የህፃናት ክብካቤ ማዕከል ጎበኙ

ቀዳማዊት እመቤት ወ/ሮ ዝናሽ ታያቸው የቁስቋም የህፃናት ክብካቤ ማዕከል የግንባታ ሂደት የደረሰበትን ደረጃ ጎብኝተዋል፡፡

በቀዳማዊት እመቤቷ የተጎበኘው የቁስቋም የህፃናት ክብካቤ ማዕከል ግንባታ በመጠናቀቅ ላይ መሆኑም ተገልጿል፡፡

ማዕከሉ ግንባታ ሲጠናቀቅ ለወ/ሮ ዘውዴ የህፃናት ክብካቤ ማዕከል ተላልፎ እንደሚሰጥም ነው ከቀዳማዊት እመቤት ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ የሚያመለክተው፡፡