በዘመን መለወጫው ደንበኞች የውሃ ችግር እንዳያጋጥማቸው እየሰራ መሆኑን ባለስልጣኑ አስታወቀ

በዘመን መለወጫው በዓል ደንበኞች የውሃ ችግር እንዳያጋጥማቸው እየሰራ መሆኑን የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን አስታወቀ፡፡

ከጳጉሜ 1 እስከ መስከረም 5 የሚቆይ በማዕከል እና በስምንቱም ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ጊዜያዊ ኮሚቴ በማቋቋም እስከ ምሽቱ 5 ሰዓት ድረስ እየሰራሁ ነው ብሏል ባለስልጣኑ፡፡

የውሃ እጥረቱን ለመቅረፍ እንዲቻል በየዕለቱ 14 ሺህ ሜትር ኪዩብ ተጨማሪ ውሃ እየተመረተ እንደሚገኝም ባለስልጣኑ ገልጿል፡፡

የኤሌትሪክ ሀይል መቆራረጥ ሲያጋጥም ከመደበኛው እንቅስቃሴ በተለየ መልኩ የጄነሬተር ቡድን በማሰማራት በቀን እስከ አምስት ሺህ ሊትር ነዳጅ እየተሞላ ነው ብሏል፡፡

የከፋ ችግር ባለባቸው አካባቢዎች ውሃን ለማድረስ የባለሥልጣኑ 24 የውሃ ቦቴዎች ዝግጁ ሆነው እየተጠባበቁ መሆናቸውም ተገልጿል፡፡