አቶ ሽመልስ አብዲሳ ለአዲሱ ዓመት የእንኳን ደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ም/ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ አዲሱን ዓመት በማስመልከት ባስተላለፉት መልዕክት 2012 ዓ.ም የህዝባችንን ተጠቃሚነት በይበልጥ የምናረጋግጥበት ዘመን ይሆናል ብለዋል፡፡

የኦሮሞ ህዝብ የክረምቱ ዝናብና ጨለማ አልፎ ወደ ጸደይ ብርሃን ሲገባ፣ ጨለማውን አሳልፎ ብርሃኑን ላሳየው ዋቃ ምስጋናን ያቀርባል፣ ለሰራው መልካም ሥራዎች ምስጋና ያደርሳል፣ የጎደለውን ለመሙላት ወደፊት ያልማል ብለዋል አቶ ሽመልስ ባስተላለፉት መልዕክት፡፡

አዲሱ ዘመን እንደ ብረት በጠነከረው አንድነት የህዝቡን ሕይወት ለመቀየር ሌት ተቀን በመትጋት የህዝቡ ፍላጎት የሚሟላበት ዘመን ይሆን ዘንድም ተመኝተዋል፡፡

አቶ ሽመልስ “አዲሱ አመት በጎ በጎውን አስበንና ሰርተን የህዝባችንን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ህይወት የምንለዉጥበትና ብሩህ ተስፋን የምንሰንቅበት ዘመን ይሁንልን” በማለት መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል፡፡