ፕሬዝዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ በቀድሞው የዚምባብዌ ፕሬዝዳንት ሮበርት ሙጋቤ የስንብት ፕሮግራም ላይ ተሳተፉ

ፕሬዝዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ ባለፈው ሳምንት ከዚህ ዓለም በሞት በተለዩት በቀድሞው የዚምባብዌ ፕሬዝዳንት ሮበርት ሙጋቤ የስንብት ፕሮግራም ላይ ተሳትፈዋል፡፡

በሀራሬ በሚገኘው ብሄራዊ የስፖርት ስታዲየም በተካሄደው ስነ ስርዓት ላይ የሀገራትና የመንግስታት መሪዎች እንዲሁም የቀድሞ ፕሬዝዳንቶችና በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ተገኝተዋል፡፡

ኢትዮጵያ በሺዎች የሚቆጠሩ የነጻነት ታጋዮችን በማሰልጠን ዚምባብዌ ከቅኝ ግዛት እንድትላቀቅ የራሷን ሚና መጫወቷ ይታወቃል፡፡

ይህ ሁኔታ ሮበርት ሙጋቤ ከኢትዮጵያ ጋር ያላቸው ቁርኝት ጥብቅ እንዲሆን የራሱን አስተዋፅዖ አድርጓል፡፡

ምንጭ፡- የፕሬዝዳንት ጽ/ቤት