ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ በኢትዮጵያ የሳዑዲ ዓረቢያ አምባሳደር ሳሚ ጀሚል አብዱላህ ጋር ተወያዩ

የሰራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ በኢትዮጵያ የሳዑዲ ዓረቢያ አምባሳደር ሳሚ ጀሚል አብዱላህ ጋር ተወያዩ።

ሚኒስትሯ ከአምባሳደሩ ጋር በሁለትዮሽና ለስራ ወደ ሳዑዲ በሚሄዱ ሰራተኞች ዙሪያ የደረሷቸውን ስምምነቶች ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መወያየታቸው ነው የተገለጸው።

በዚህ ወቅትም አምባሳደሩ ተቋርጦ የነበረው የውጭ ሃገር የስራ ስምሪት ዳግም እንዲጀመር ላደረጉት ጥረት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

አምባሳደር ሳሚ ጀሚል በበኩላቸው፣ ሚኒስቴሩ ህገ ወጥ የስራ ስምሪትን በመከላከል ህጋዊ የስራ ስምሪት እንዲኖር ያደረገውን ጥረት አድንቀዋል።

አያይዘውም ሀገራቸው ኢትዮጵያውያን ዜጎች በሳዑዲ ህጋዊ ሆነውና ደህንነታቸው ተጠብቆ እንዲሰሩ ድጋፍ ማድረጓን አብራርተዋል።

ከውይይቱ በኋላም ሀገራቱ ለስራ ወደ ሳዑዲ በሚሄዱ ዜጎች አጠቃላይ ሁኔታ በጋራ ለመስራትና መረጃ ለመለዋወጥ መስማማታቸውን ከሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።