የኢሬቻ የጎዳና ሩጫ የፊታችን እሁድ ይካሄዳል

“የሆራ ፊንፊኔ” የኢሬቻ ሩጫ እሁድ መስከረም 11 ቀን 2012 ዓ.ም በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ የኦሮሚያ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ አስታወቀ።

ሩጫው መስከረም 24 ቀን 2012 ዓ.ም በአዲስ አበባ የሚከበረውን የኢሬቻ በዓልን ምክንያት በማድረግ የሚካሄድ እንደሆነ ተገልጿል፡፡

በዚህ የሩጫ ውድድር ላይ ከ50 ሺህ በላይ ሰዎች ይሳተፉበታል ተብሎ እንደሚጠበቅ የኦሮሚያ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ አድማሱ ዋቅጋሪ ለኢዜአ ተናግረዋል። 

እንደ አቶ አድማሱ ገለጻ የሩጫው ቲ-ሸርት በፌዴራልና በክልሉ በመሰራጨት ላይ ያለ ሲሆን፣ ሽያጩም አንዱ ቲ-ሸርት በ250 ብር እየተካሄደ ይገኛል።

የቲ-ሸርቱ የመሸጫ ቦታዎች በፌዴራልና በክልሉ መስሪያ ቤቶች የሚገኙ ሰራተኞች እንዲሁም በፊንፊኔ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞንና በአዲስ አበባ የሚገኙ ነዋሪዎች ከኦሮሞ ባህል ማዕከል ማግኘት እንደሚችሉ ተናግረዋል።

በክልሉ ሌሎች ዞኖች የሚገኙ ነዋሪዎች ደግሞ በዞን እና በወረዳ እንዲሁም በሁሉም ከተሞች ባሉት የባህልና ቱሪዝም ቢሮዎች ማግኘት ይችላሉ ብለዋል።