የዘንድሮ ኢሬቻ በዓልን ለማክበር ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁ ተገለጸ

የ2012 ዓ.ም የኢሬቻ በዓልን ለማክበር ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁን የኦሮሚያ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ አስታወቀ፡፡

ቢሮ በዛሬው ዕለት ለመገናኛ ብዙሃን በሰጠው መግለጫ እንዳስታወቀው; በመስከረም 24፤ 2012 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከአንድ ምዕተ አመት በኋላ የሚከበረውን የሆራ ፊንፊኔ እና በማግስቱ መስከረም 25 በቢሾፍቱ ሆራ አርሰዲ የሚከበረው የኢሬቻ በዓል ባህላዊና ትክክለኛ እሴቱን ጠብቆ እንደሚከበርተገልጿልl፡፡

በተለይም በመስከረም 24፤2012 ዓ.ም በአዲስ አበባ የሚከበረው ኢሬቻ ፊንፊኔ ለከተማው ነዋሪዎች ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ የሚሰጥና ኢሬቻን እንደ ገዳ ስርዓት ሁሉ በዩኒስኮ ለማስመዝገብ የሚደረገው ጥረት ስኬታማ እንዲሆን ትክክለኛና ባህላዊ እሴቱ ተጠብቆ እንዲከበር ይደረጋልም ተብሏል፡፡

በበዓሉ አከባበርም ኢሬቻን ለሰላም የሚል ታላቅ ሩጫን ጨምሮ የኢሬቻ ፎረም፣ እግዝቪሽንና የኦሮሞ ህዝብ የተለያዩ ባህላዊ ትርዕቶች ለማቅረብ ዝግጅት መጠናቀቁ በመግለጫው ተገልጿል፡፡

በበዓሉ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳታፊ እንደሚሆኑ ይጠበቃል፡፡