የአማራ ምሁራን መማክርት ጉባኤ ምክክር በባሕር ዳር እየተካሄደ ነው

የአማራ ምሁራን መማክርት ጉባኤ በክልሉ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ዙሪያ የሚመክር ዓለም አቀፍ የምክክር መድረክ  በባሕር ዳር ማካሄድ ጀምሯል፡፡

ጉባኤው የአማራ ሕዝብ የፍትሕ፣ የሠላም እና የነፃነት ተጠቃሚነት ለኢትዮጵያ አንድነት በሚፈጥርባቸው ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነው፡፡

የአማራ ሕዝብ በሚያነሳቸው ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊ እና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ምክክሩ ትኩረት እንደሚያደርግ የታወቀ ሲሆን፤ ለሁለት ቀናትም ይቆያል፡፡

በውይይቱ 1 ሺህ 800 ምሁራንና ከ700 በላይ ተጋባዥ እንግዶች እንደሚገኙ ታውቋል፡፡

ለውይይቱ መነሻ የሚሆኑ አራት ጥናታዊ ጽሑፎችም ቀርበው ውይይት እየተካሄደባቸው ይገኛል፡፡

በውይይቱ የተለዩ ችግሮችን ለመፍታት በቀጣይ እስከ ቀበሌ ድረስ ከሚገኙ የማኅበረሰብ ክፍሎች ጋር ውይይት እንደሚደረግ አብመድ ነው የዘገበው፡፡