የኢሬቻ በዓል ሩጫ በሰላም እንዲፈፀም ዝግጅት ማጠናቀቁን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ

 የኢሬቻ በዓልን ምክንያት በማድረግ በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ የሚካሄደው ሩጫ በሰላም ተጀምሮ እንዲጠናቀቅ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት አጠናቆ ወደ ስራ መግባቱን አስታወቋል፡፡

መስከረም 11 ቀን 2012 ዓ/ም መነሻና መድረሻውን መስቀል አደባባይ የሚያደርገዉና ከ50 ሺህ ሰው በላይ ይሳተፍበታል ተብሎ የሚጠበቀው “ኢሬቻ ለሰላም” በሚል መሪሃሳብ የሚካሄደው የጎዳና ላይ ሩጫ በሰላም እንዲጠናቀቅ ዝግጅት ጨርሶ ወደ ሰራ መገባቱን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮማንደር ፋሲካ ፋንታ ገልፀዋል፡፡ 

ኮማንደር ፋሲካ ህብረተሰቡ ከዚህ በፊት የተደረጉ ልዩ ልዩ የአደባባይ ኩነቶች በሰላም እንዲጠናቀቁ በትዕግስት፣ በኢትዮጵያዊ ጨዋነትና በመደጋገፍ ላሳየው ቀና ትብብር የአዲስ አበባ ኮሚሽን ምስጋናውን ያቀርባል ብለዋ፡፡

 ኮማንደር ፋሲካ ፋንታ  የ“ኢሬቻ ለሰላም” የጎዳና ላይ ሩጫ ከመስቀል አደባባይ በመነሳት በለገሃር ፣ ቡናና ሻይ ፣ ገነት መብራት፣ ቡልጋሪያ ማዞሪያ ፣ ቄራ ጎተራ ፣ አጎና ሲኒማ ፣ ግሎባል ሆቴል እና በመሿለኪያ አድርጎ ስለሚካሄድ ከዋዜማው ጀምሮ እስከ ሩጫው ፍፃሜ ድረስ በእነዚህ መስመሮች ላይ ለረዥምም ሆነ ለአጭር ጊዜ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ በፍፁም የተከለከለ በመሆኑ ህብረተሰቡ  የትራፊክ ፖሊስ አባላት እና የፀጥታ አካላት የሚሰጡትን ትዕዛዝ በማክበር የተለመደ ትብብር እንዲያርግ ኮሚሽኑ ይጠይቃል ብለዋል፡፡

ውድድሩ ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ፡-

  • ከቅዱስ ኡራኤል ቤተ ክርስቲያን ወደ መስቀል አደባባይ
  • ከኦሎምፒያ ወደ መስቀል አደባባይ
  • ከአራት ኪሎ ወደ መስቀል አደባባይ
  • ከሃራምቤ ሆቴል ወደ መስቀል አደባባይ
  • ከልደታ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ
  • ከዋቢ ሸበሌ ሆቴል ወደ ቄራ
  • ከአፍሪካ ህብረት አደባባይ ወደ ቡልጋሪያ ማዞሪያ
  • ከሳር ቤቶች አደባባይ ወደ ቄራ
  • ከጎፋ ገብርኤል ወደ ጎፋ ማዞሪያ
  • ከቂርቆስ አዲሱ መንገድ ወደ ጎፋ ማዞሪያ
  • ከቂርቆስ አዲሱ መንገድ ወደ ለገሃር
  • ከቂርቆስ ወደ ገነት ሆቴል
  • ከመስቀል ፍላወር ወደ አጎና ሲኒማ የሚወስዱ መንገዶች ለጊዜው ለተሽከርካሪ ዝግ በመሆናቸው
  • ከኡራኤል ወደ ጦር ይሎች አደባባይ መሄድ የሚፈልጉ አሽከርካሪዎች
  • E አራት ኪሎE ሸራተን አዲስE ሃራምቤ ሆቴልE ጎማ ቁጠባ
  • ከፒያሳ ወደ ቦሌ መሄድ የሚፈልጉ አሽከርካሪዎች
  • ሆቴል E ፍል ውሃE ካዛንቺስE ኡራኤልE አትላስ ሆቴልEቦሌ
  • ከሳር ቤት ወደ ልደታ ከፍተኛ /ቤት መሄድ የሚፈልጉ አሽከርካሪዎች
  • አቦ መታጠፊያE መድሃኒት ፋብሪካE ሦስት ቁጥር ማዞሪያE ብስራተ- ገብርኤል አቅጣጫE በካርል አደባባይE ቴሌE ልደታ ከፍተኛ ፍ/ቤት የለውን መስመር መጠቀም ይቻላሉ ብሏል፡፡