550 ኮንቴነር መድኃኒቶችና የሕክምና ግብዓቶች መግባታቸውን የኢትዮጵያ መድሃኒት አቅራቢ ድርጅት አስታወቀ

የኢትዮጵያ መድሃኒት አቅራቢ ድርጅት ባለፋት 2 ወራት ከ550 ኮንቴነር በላይ መድኃኒቶችንና የሕክምና መገልገያ ግብዓቶችን ከሞጆ ደረቅ ወደብ ማንሣቱን አስታወቀ፡፡

ከ25 ዓይነት በላይ መድኃኒቶችን ከሞጆ ደረቅ ወደብ ባጠረ ጊዜ ውስጥ ለማንሳት መቻሉን የኤጀንሲው የመድኃኒት ኮንትራት አስተዳደር ባለሙያ ወ/ሮ አጋር ተስፋዬ ገልጸዋል፡፡

መድኃኒቶቹ ለኤች.አይ.ቪ፣ ለሆድ ሕመም፣ ለኢንፌክሽን፣ ለስነተዋልዶ እና ለሌሎች አገልግሎት የሚውሉ መድኃኒቶች፣ የሕክምና መገልገያ መሣሪያዎችና ሪኤጀንቶች እንደሆኑ ወ/ሮ አጋር አብራርተዋል፡፡

መድሀኒቶቹን በቀጥታ በተለያዩ ቅርንጫፎችና በዋናው መ/ቤት የመድኃኒት ማከማቻ መጋዘን እንደገቡ አስረድተዋል፡፡

ወደ ቅርንጫፍ ቀጥታ መሄዱም ጊዜንና ወጪን በመቆጠብ ለማህበረሠቡ በቶሎ መድኃኒቶችን ተደራሽ ለማድረግ ወሣኝ ሚና አለው ሲሉ ባለሙያዋ አክለዋል፡፡

እክሎች እንዳይከሠቱ በባንኩ፣ በሞጆ ደረቅ ወደብ፣ በኢትዮጵያ የምግብና የመድኃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን እና በኤጀንሲው መካከል ውል ለመፈራረም በዝግጅት ላይ መሆናቸውንም ባለሙያዋ ገልፀዋል፡፡

(ምንጭ፡- የኢትዮጵያ መድሃኒት አቅራቢ ድርጅት)