ዋና ሳጅን ሲራጅ አብደላ ከፌዴራል ፖሊስ ስማርት ስልክ እና የምስክር ወረቀት ተበረከተለት

በአፋር ህገ ወጥ መሳሪያን በገንዘብ ተደልሎ አላሳልፍም ያለው ዋና ሳጅን ሲራጅ አብደላ ስራው አርአያነት ያለው ነው በሚል የፈደራል ፖሊስ ኮሚሽን በዛሬው ዕለት እውቀና ሰጥቶታል።

ዋና ሳጅን ሲራጅ አብደላ ከፌደራል ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር ጄኔራል መላኩ ፋንታ እጅ የስማርት ስልክ እና የእውቅና ምስክር ወረቀት ተቀብሏል።

ምክትል ኮሚሽነሩ ፖሊሱ በሰራው አኩሪ የህግ ማስከበር ስራ አርዓያ በመሆኑ በኮሚሽኑ ስም ምስጋና አቅርበውለታል።

ዋና ሳጅን ሲራጅ አርዓያነት ላለው ተግባሩ ከአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባና ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድም እውቅና መሰጠቱ ይታወሳል።