የራስ መኮንን ፓርክ ተመረቀ

በአዲስ መልክ ለህብረተሰቡ አገልግሎት እንዲሠጥ የተደራጀውን የራስ መኮን ፓርክ የአዲስ አበባ ም/ከንቲባ ኢ/ር ታከለ ኡማ መርቀው ስራ አስጀምረውታል፡፡

ከ4 ሺህ 300 ካ.ሜ በላይ ስፋት ያለው የራስ መኮንን ፓርክ የአረንጓዴ ቦታን ጨምሮ የህፃናት መጫወቻ ስፍራ እና ለአከባቢው ወጣቶች የስፖርት ማዘውተሪያ ማዕከልን ያካተተ ነው፡፡

ከራስ መኮንን ፓርክ በተጨማሪ ጦር ኃይሎች አከባቢ የሚገኘው ሆላንድ ፓርክ (65 ሺህ ካ.ሜ) እና የአቃቂ ፓርክ (62 ሺ ካ.ሜ) በተመሳሳይ መልኩ ለህብረተሰቡ አገልግሎት እንዲሠጡ ተመርቀው ወደ ስራ ገብተዋል፡፡

በዛሬው ዕለት የተመረቁት 3 ፓርኮች በአጠቃላይ 13.9 ሔክታር በላይ ስፋት ያላቸው ናቸው፡፡

በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ ኢ/ር ታከለ ኡማ ራስ መኮንን ፓርክ ውስጥ ያለውን የስፖርት ማዘውተሪያ ማዕከል በማህበር ለተደራጁ የአከባቢው ወጣቶች አስረክበዋል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ ጤናማ እና አረንጓዴ አዲስ አበባን ለመገንባት ትላልቅ ፕሮጀክቶችን ነድፎ እየሰራ እንደሆነ ተገልጿል፡፡

(ምንጭ፦ ከንቲባ ፅ/ቤት)