የተለያዩ እምነት ተከታዮች ከኢ/ር ታከለ ጋር መስቀል አደባባይን አፀዱ

የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ ከተለያዩ እምነት ተከታዮች ጋር መስቀል አደባባይን አፅድተዋል፡፡

ዛሬ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች የሚከበረውን የደመራ በዓልን አስመልክቶ የከተማ ነዋሪዎች በዓሉ የሚከበርበትን ስፍራ እንዲያፀዱ ምክትል ከንቲባው ጥሪ ማቅረባቸው ተከትሎ ነው ፅዳቱ የተካሄደው፡፡

ዛሬ ከማለዳ ጀምሮ በተካሄደው የፅዳት ዘመቻ ላይ የእስልምና እምነት ተከታዮችን ጨምሮ በርካታ የከተማው ነዋሪዎች መሳተፋቸውን ከከንቲባ ፅ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

የደመራ በዓል የሀይማኖት መሪዎች፣ በርካታ የእምነቱ ተከታዮችና የውጭ ሀገራ ጎብኚዎች በተገኙበት በመስቀል አደባባይ ዛሬ በታላቅ ስነ-,ስርዓት ይከበራል፡፡