በአሰላ ተከስቶ የነበረው ግጭት በባህላዊ የእርቅ ሥነ-ሥርዓት ተፈታ

በአርሲ አሰላ ከተማ አስተዳደር ተከስቶ የነበረው ግጭት በባህላዊ የእርቅ ሥነ-ሥርዓት ተፈትቷል፡፡

ከዚህ ቀደም አጋጥሞ የነበረውን ግጭት አባ ገዳዎች እና የሀገር ሽማግሌዎች ከከተማ አስተዳደሩ ጋር በጋራ በመሆን የእርቅ ውይይት ሲካሄድ ቆይቶ አሁን ላይ ከኅብረተሰቡ ጋር የእርቁ የማጠቃለያ ሥነ-ሥርዓት ተከናውኗል።

በተሳሳተ መረጃ የተፈጠረውን አለመግባባት የሃይማኖት ግጭት ለማስመሰል ተሞክሮ እንደነበረም ተገልጿል።

በተከሰተው ግጭት የአንድ ሰው ሕይወት ሲጠፋ የአካል ጉዳት እና የንብረት ውድመትም ደርሷል።

በዚህ ግጭት መነሻነት የኅብረተሰቡ የእርስ በርስ ግንኙነት ተቀዛቅሶ እንደነበረ እና አሁን ላይ የተደረገው እርቀ-ሰላም ግንኙነቱን ወደነበረበት እንደሚመልሰው መገለፁን ኢቢሲ ዘግቧል።