የወላይታ ብሔር ዘመን መለወጫ ጊፋታ በዓል እየተከበረ ነው

ከመስከረም 15 ጀምሮ እየተከበረ ያለው የወላይታ ብሔር ዘመን መለወጫ ጊፋታ በዓል በዛሬው እለት መስከረም 18 ቀጥሎ በደማቅ ስነ-ስርአት እንደሚከበር ተገለፀ።

የወላይታ ብሔር ዘመን መለወጫ የጊፋታ በዓል በዛሬው እለት ተጋባዥ እንግዶች በሚገኙበት በተለያዩ ደማቅ ስነስርዓቶች እንደሚከበር የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዳጋቶ ኩምቤ ገልፀዋል።

ጊፋታ አዲስ ዓመትን አሀዱ ብሎ የሚጀምርበት የአዲስ ዓመት መግቢያ ብቻም ሳይሆን የብርሃን ጊዜ ማብሰሪያ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡

በዓሉ በየዓመቱ በሚከበርበት ወቅት ወጣቶች፣ ሴቶች እና ሌሎች የማህበረሰብ ክፍሎች በዓሉን በተለያዩ ስነ ስርዓቶች ያከብሩታል፡፡

የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዳጋቶ ኩምቤ እና የዞኑ በህል ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ ሃላፊ አቶ ፀጋው ስምኦን በዓሉን በማስመልከ ለጋዜጠኞች በስጡት መግለጫ የዘንድሮ የጊፋታ በዓል ከሌላው ጊዜ በተለየ መልኩ እየተከበረ መሆኑን ተናግረዋል።

የወላይታ ብሔር ዘመን መለወጫ ጊፋታ በዓልን ምክንያት በማድረግ ለጊፋታ እሮጣለሁ በሚል የተዘገጀ የ3ኪሎ ሚትር የሩጫ ውድድር መካሄዱ ይታወሳል፡፡