የሀዋሳ ከተማ ደረቅ ቆሻሻ ማስወገጃ በኑሯቸው ላይ እክል እየፈጠረ መሆኑን ነዋሪዎች ገለጹ

የሀዋሳ ከተማ ደረቅ ቆሻሻ ማስወገጃ ቦታ በጤናቸው ላይ እክል እየፈጠረ መሆኑን ነዋሪዎች ገለጹ፡፡

ስምንት ክፍለ ከተሞችና 32 ቀበሌዎች ያሏት ሀዋሳ ከከተማ መስፋፋት ጋር ተያይዞ ቆሻሻ መስገጃው ለመኖሪያ ቦታዎች ይበልጥ እየተጠጋ ነው፡፡

በመሆኑም በከተማዋ በተለምዶ ዳያስፖራ ተብሎ የሚጠራው አካባቢ ነዋሪዎች በቆሻሻው ምክንያት ለልዩ ልዩ የመተንፈሻ አካላት ችግሮች መጋለጣቸውን በህክምና ማስረጃ አስደግፈው ለዋልታ አስረድተዋል፡፡

ከክልሉ ርእሰ መስተዳድር ጀምሮ እስከ ክፍለ ከተማ ድረስ ላለፉት ሰባት ዓመታት ቢያመለክቱም ሰሚ ማጣታቸውን ነዋሪዎቹ ተናግረዋል፡፡

ጉዳዩን በተመለከተ ምላሽ የሰጡት የከተማዋ ከንቲባ ጥራቱ በየነ አዲሱ አመራር ለነዋሪዎቹ ቅሬታ ቅድሚያ በመስጠት የ45 ቀናት የድርጊት መርሃ ግብር አውጥቶ እየሰራ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

ከከተማ እድገት ጋር ተያዞ አሁን ያለው ደረቅ ቆሻሻ ማስወገጃ ስፍራ በአዲስ ለመተካት የዲዛይን ስራ መጠናቀቁንም ከንቲባው ገልፀዋል፡፡