የአፍሪካ ልማት ባንክ የ12 ቢሊየን ዶላር የኤሌክትሪክ ኃይል ፕሮግራምን ይፋ አደረገ

የአፍሪካ ልማት ባንክ በአጠቃላይ 12 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር ወጪ  የአፍሪካን በኤሌክትሪክ መሠረተ ልማት ለማስተሳሰር የሚያስችለውን  ፕሮጀክቱን ይፋ አድርጓል፡፡

ፕሮጀክቱ በአምስት አመታት ውስጥ ተግባራዊ እንደሚሆንም ነው ልማት ባንኩ ባወጣው  መረጃ የልማት ባንክ አስታወቀ ።

ፕሮጀክቱ ቀደም ብሎ በዕቅድ የተያዘና እኤአ በ2025 በሁሉም የአፍሪካ ሀገራት የተሻለ የኃይል ትስስር እንዲፈጠር ለማስቻል የተቀመጠው ግብን ለማሳካት ያለመ ፕሮጀክት  እንደሆነም ተጠቅሷል፡፡   

ባለፈው ወር በኮትዲቯር በተካሄደውና የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በተገኙበት የኤሌክትሪክ ኃይል ሳምንት ኮንፈረንስ ላይ ነው የ12 ቢሊዮን ፕሮጀክት ትግበራ ይፋ ተደርጓል ፡፡

ከቅርብ ዓመታት አፍሪካ ለታዳሽ ኃይል እየሰጠች ያለችው ትኩረትና የዘረፉ ተወዳዳሪ እየሆነ መምጣትም እንደ አፍሪካ ልማት ባንክ ያሉ የልማት ተቋማት አፍረካን በኃይል ማስተሳሰር ላይ በስፋት እንዲሳተፉ እያደረገ ይገኛል ተብሏል፡፡

በቀጣይ አምስት ዓመታት ይተገበራል የተባለው ፕሮጀክት የፀሃይ ኃይልን በታዳሽ የኃይል አማራጭነት በተለይም በገጠር አካባቢዎች ላይ በስፋት ለመጠቀም ግብ መጣሉም ነው የተመለከተው፡፡

ቀደም ሲል ከእስያ ሀገራት ተመርተው ወደ አፍሪካ በተለይም ወደ ምስራቅ አፍሪካ ይገቡ የነበሩና የፀሃይ ኃይልን ወደ ኤሌክትሪክ ኃይል መለወጥ የሚያስችሉ መሣሪያዎች አሁን እጅግ በዝቅተኛ ዋጋ በአፍሪካ ለገበያ መቅረባቸው ምን ያህል የፀሃይ ኃይል በማህበረሰቡ ዘንድ ተቀባይነት እያገኘ ስለመምታቱ ማሳያ  መሆኑ  ተጠቁሟል ፡፡

የአፍሪካ ልማት ባንክ  ፕሬዚደንት አኪንውሚ አዲሲና እንደሚገልጹት  የኃይል ፕሮጀክቶችን በመደገፍ ረገድ  የግሉ ክፍለ ኢኮኖሚ ሰፊ ድርሻ ቢኖረውም በተለይም እንደ ኢትዮጵያ ያሉ የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ተቀናጅተው በብሔራዊ ደረጃ የኃይል ትስስር እንዲጠናከርና  የሚሆዱበት  ርቀትም  አበረታቸው ነው ብለዋል ።

የአፍሪካ ልማት ባንክ በአፍሪካ የታዳሽ የኃይል ምንጮች በስፋት በሥራ ላይ እንዲውሉ  ትኩረት  ሠጥቶ እየሠራ ይገኛል ።