የአፍሪካ ኩባንያዎች መሪዎች ፎረም በሩዋንዳ መካሄድ ጀመረ

የአፍሪካ ኩባንያዎች መሪዎች ፎረም ለ7ኛ ጊዜ በሩዋንዳ ርዕሰ መዲና ኪጋሊ ዛሬ መካሄድ ጀምሯል፡፡

የአፍሪካ ኩባንያ መሪዎች ፎረም የአፍሪካን የግሉን ዘርፍ በስፋት የሚያሳትፍ እና የግሉ ዘርፍ ተግዳሮቶች እንዲሁም ዕድሎች ዙሪያ የሚመክር በአህጉሪቱ ከሚካሄዱ ትላልቅ የዓለም አቀፍ መድረኮች አንዱ ነው፡፡

ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴም በዓለማቀፍ ደረጃ ታወቂ የሆኑ ኩባንያ እና የአገራት መሪዎች በተወከሉበት በዚህ መድረክ ላይ እየተሳተፉ ነው፡፡

መድረኩ አገራት ያላቸውን የኢንቨስትምንት አማራጮችን ለማስተዋወቅ እድል የሚፈጥር ነው፡፡

ኢትዮጵያም መድረኩን የግሉን ዘርፍ ለማሳተፍ አገሪቱ እያከነወነች ያለውን ተግባርና ያሏትን የኢንቨስትመንት አማራጮችን ለማስተዋወቅ ትጠቀምበታለች ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የአፍሪካ ኩባንያዎች ፎረም ከአውሮፓወያኑ 2012 ጀምሮ በተለያዩ የአህጉሪቱ ከተሞች የተካሄደ ሲሆን በአፍሪካ ኢኮኖሚ ላይ የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ ለማሳደግ ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ ያለ አለማቀፍ ኮንፍረንስ ነው፡፡ (ኢቲቪ)