ኬንያ በ210 ሚለዮን ዶላር የባቡር መስመሮቿን ልታድስ ነው

ኬንያ 210 ሚለዮን ዶላር በሆነ ወጪ የባቡር መስመሮቿን  ልታድስ  መሆኑ አስታወቀች ፡፡

ኬንያ  የባቡር መስመሮቿን ለማጠናከር እና ያረጁ የባቡር ፍርጎዎችን በአዲስ ለመተካት እየሰራች ትገኛች፡፡

ደረጃውን በጠበቀ መልኩ የባቡር መስመሮቿን ለማገናኘት እና ለማጠናከር 210 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ወጪ ልታደርግ መሆኑ ተሰምቷል፡፡

ቻይና ለዚህ ፕሮጀክት ወጪ ፈንድ እንደምታደረግ ነው የተነገረው ፡፡

በቻይና የገንዘብ ድጋፍ የሚሰራው ይህ የባቡር ፕሮጀክት  ከኡጋንዳ ጋር ያላትን ድንበር በማያያዝ በህንድ ውቅያኖስ ዙሪያ ካሉ ጎረቤት ሀገራት ጋር ፈጣን የንግድ ግንኙነትን ለመፍጠር ያስችላል ተብሎ ይጠበቃል ፡፡

ለፕሮጀክቱ  ከተመደበው ገንዘብ ውስጥ  60 ሚሊዮን ዶላሩ  የ43 ኪሎሜትር ርዝመት ወይም 26.7 ማይል  የሚሸፍነውን አሮጌውን የባቡር መስመር አዲስ ከሚሰራው ጋር የሚያገናኘውን መስመር ለመዘርጋት ይውላል ያሉት  የትራንስፖርትና የመሠረተ ልማት ሚኒስቴር ሚስትር ጀምስ ማቻሪያ ናቸው ፡፡

ሚኒስትሩ በናይሮቢ ለጋዜጠኖች በሰጡት መግለጫ አማራጭ የባቡር መስመሮች ያስፈልጉናል ለዚህ ስራ የግሉ ዘርፍን እንበርጣለን ይህም በሀገሪቱ እዳ ላይ ምንም ተጽእኖ እንዳይኖር ይረዳናል ፡፡

ይህ የባቡር መስመር ዝርጋታ ለመጠናቀቅ አንድ አመት ያህል ጊዜ ይወስዳል በዚህ ወቅት የባቡር ፍረጎዎቹም አብረው የሚሰሩ ይሆናል ነው ያሉት ፡፡

ይህ እንቅስቃሴ ለኬኒያውያን የለውጥ ጉዞ ነው፡፡ እቅዱም  ደረጃውን የጠበቀ የባቡር መጓጓዣው መንገድ በመዘርጋት  በመካከለኛው ምስራቅ አፍሪካ ከሚገኘው የሞምባሳ ወደብ እስከ  ኡጋንዳ ድረስ ያላውን የንግድ ትስስር ለማጠናከር ያለመ ነው ፡፡

በተመሳሳይም  ኡጋንዳ 152 ሚሊዮን ዩሮ ወይም 170.3 ሚልዮን ዶላር በሆነ ወጪ   ከማላዋ ወደ ካምፓላ ያለውን ነባር የባቡር  መስመር በአዲስ መልክ  ደረጃውን ከፍ ለማደርግ እንደምትሰራም ተገልፁዋል ፡፡

(ምንጭ ፡- ሲጂቲኤን)