ቦትስዋና ዝሆን ማደን ፈቀደች

ቦትስዋና ለአምስት አመታት በዝሆን አዳኞች ላይ ያወጣችውን እገዳ ማንሳቷን ገለጸች።
የቦትስዋና የአከባቢ፣ የተፈጥሮ ጥበቃ እና የቱርዝም ሚኒስቴር ለአምስት አመት በዝሆኖች አደን ላይ ተጥሎ የነበረው እገዳ መነሳት አግባብ እንደሆነ ነው የገለጸው።

የዱር እና የብሔራዊ ፓርክ ቁጥጥር ባለስልጣን አደኑ በሥርዓት እና በሥነ-ምግባር የተደገፈ እንዲሆን ሚኒስቴሩ ከሁሉም ባለድርሻ አካላት ጋር አብሮ መስራት እንዳለበት ገልፅዋል። 

የሀገሪቱ መንግስት እ.ኤ.አ ሰኔ 2018 ኮሚቴ በማቋቋም ማህበረሰቡን በማወያየት የጋራ መግባባት ላይ በመድረሱ ነው እገዳውን ያነሳው።

እንደ ሪፖርቱ ገለጻ በአደን ላይ እገዳ በመደረጉ የዝሆኖቹ ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ የጨመረ ሲሆን፣ ይህም የሰው ልጅ ከዝሆኖች ጋር ወደ ግጭት ውስጥ ሊያሰገባው እንደሚችል በመረጃው ሰፍሯል።

የቦትስዋና ጎረቤት ሀገራት ዝሆን ማደን በእያንዳንዱ አደን በአማካኝ ወደ 45 ሺህ አሜሪካ ዶላር በህግ ያስቀጣል።

ቦትስዋና ከአለም በዝሆኖች ቁጥር ከፍተኛውን ድርሻ እንደምትይዝ ይታወቃል፡፡

ቦትስዋና በአፍሪካ ውስጥ ለዝሆኖች አስተማማኝ እና ምቹ ከሆኑ ቦታዎች አንዱ በመሆና አንዳንድ የአካባቢ ጥበቃ ባለሙያዎች ይህን እንቅስቃሴ በመቃወም ላይ ይገኛሉ ሲል ዩፕአይ በዘገባው አስፍሯል።