የመጀመሪያው የቻይና አፍሪካ የንግድና የኢኮኖሚ ኤክስፖ ተጀመረ

የመጀመሪያው የቻይና – አፍሪካ የንግድና ኢኮኖሚ ኤክስፖ በማእከላዊ የቻይናዋ ሁዋን ግዛት ቻንግሻ ከተማ ነው የተከፈተው፡፡

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የኢንዱስትሪ ልማት፣ የዓለም የምግብ ፕሮግራም እንዲሁም የዓለም ንግድ ድርጅት በኤክስፖው ላይ የሚሳተፉ ተወካዮቻቸውን ልከዋል፡፡

የግብርና፣ ንግድ፣ ኢንቨስትመንት እና መሰረተ ልማት ግንባታ የሚሉ ዘርፎች በኤክስፖው ላይ የሚቀርቡ ዝግጅቶች መሆናቸው ተገልጿል፡፡

ለ3 ቀናት የሚቆየው ይህ ኤክስፖ ከ53 የአፍሪካ አገራት ወደ 10 ሺህ የሚጠጉ እንግዶችንና የንግዱን ማህበረሰብ ያሳተፈ እንደሆነ ነው አዘጋጅ ኮሚቴው ያስታወቀው፡፡/ሺንዋ/