ደቡብ አፍሪካ የቡድን 20 ጉባኤ ላይ ለታዳጊ አገራት ድጋፍ እንዲያገኝ እንደምትሰራ አስታወቀች

ደቡብ አፍሪካ የቡድን 20 ጉባኤ ላይ ለታዳጊ አገራት የሚደረገው ድጋፍ ትኩረት እንዲያገኝ እንደምትሰራ አስታወቀች 
ደቡብ አፍሪካ በጃፓን በሚደረገው የቡድን 20 ጉባኤ ላይ በአፍሪካና በማደግ ላይ ባሉ አገራት ውስጥ ለዘላቂ የልማት ግቦች የሚደረገው ድጋፍ ትኩረት እንዲያገኝ ለማድረግ አጋጣሚውን እንደምትጠቀም የአገሪቱ ፕሬዝዳንት ቃል አቀባይ ኩሴላ ዲኮ ገልጸዋል፡፡

የጉባኤው አጀንዳዎች አለም አቀፍ ምጣኔ ሃብት፣ ንግድ፣ ኢንቨስትመንት፣ ፈጠራ፣ የአከባቢ ጥበቃና ኃይል፣ የስራ እድል ፣ ሴቶችን ማብቃት፣ ልማት እና ጤና እንደሆኑ ለማወቅ ተችሏል፡፡

ጉባኤው ለሁለት ቀናት እንደሚደረግ ሽንዋ ዘግቧል፡፡