ኬንያ አዲስ ቋሚ የመንግስት ሰራተኞች ቅጥር ማቆሟን ገለጸች

ኬንያ ለቀጣዮቹ 3 ዓመታት የሀገሪቱን ወጪ ለመቀነስ ሲባል አዲስ ቋሚ የመንግስት ሰራተኞችን መቅጠር ማቆሟን የኬንያ ፋይናንስ ሚኒስቴር ሚኒስትር ኡኩር ያታኒ ገልጸዋል፡፡

በውሳኔው ከቅጥሩ ባሻገር ለቢሮ አገልግሎት በመንግስት በጀት በሚገዙ የተለያዩ የአይሲቲ ቁሳቁሶች ላይም እገዳ ጥሏል፡፡

ሁሉም የመንግስት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች የሚያደርጓቸውን ማንኛውም ክፍያዎችም በፋይናንስ ሚኒስቴር በኩል እንዲያልፉም ተወስኗል፡፡

በዚህ እርምጃ የሚቆጠበው ገንዘብ ለቤት ግንባታ፣ ለምግብ አቅርቦት፣ ለጤና አቅርቦት፣ ለመሰረተ ልማት ግንባታና ለተመረጡ የመንግስት ፕሮጀክቶች ስራ እንደሚውል ነው የተገለጸው፡፡ (ምንጭ፡- ቢቢሲ)