በሶማሊያ የባህር ሽፍታዎች የታገቱ 26 ሰዎች ተለቀቁ

በሶማሊያ የባህር ሽፍታዎች ታግተው የቆዩ 26 ሰዎች ነፃ መውጣታቸውን ጉዳዮን በሽምግልና ይዘው ደፋ ቀና ሲሉ የነበሩ አለማቀፍ አደራዳሪዎች አስታወቁ፡፡

ለአምስት ዓመት ገደማ በሽፍታዎቹ የተያዙት ታጋቾችም ሁሉም ወንዶች ሲሆኑ የካምቦዲያ፣ ቻይና፣ ታይዋን፣ ኢንዶኔዢያ፣ ፊሊፒንስና የቬትናም ዜጎች መሆናቸውንም ቢቢሲ በዘገባው አስፍሯል፡፡  

የታጋቾቹን የጤንነት ሁኔታን ለማወቅ በተደረገ ጥረትም ከሽፋቶቹ በተላከ የፎቶ ምስል እንጂ በአካል ለማየት እንዳልተቻለ ተመልክቷል፡፡

በፎቶዎቹም ሰዎቹ በጣም ከሲታና በምግብ እጥረት የተሰቃዩ በመሆኑ በአስቸኳይ የህክምና ድጋፍ ማግኘት አለባቸው ነው የተባለው፡፡   

ታጋቾቹን ነፃ ለማውጣም በሶማሊያ የሚገኙ  የጎሳ መሪዎች መሳተፋቸው  ታውቋል፡፡

ይሁንና ታጋቾቹን ለማስፈታት ገንዘብ ለሽፍቶቹ መከፈሉን በተመለከተ ምንም የተባለ ነገር የለም፡፡ 

ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በሶማሊያ የባህር ወደብ ላይ የሚደረጉ የሽፍቶች ዝርፊያ በእጅጉ መቀነሱን ዘገባው ጠቅሷል-( ኢብኮ) ፡፡