ዩናይትስ ስቴትስ በአልሻባብ ላይ የአየር ጥቃት ፈጸመች

ዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ በሶማሊያ በሚገኘው  የአልሻባብ አሸባሪ ቡድን ላይ የአየር ጥቃት መፈጸሟን  የፔንታጎን  ፕሬስ ሴክሬተሪ  አድሚራል  ጆን ኪርቤይ  አስታወቁ ።

የዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ የጮር ጄቶች  ድብደባ  የፈጸሙት  በሶማሊያ ሳኮው በተባለ ሥፍራ ላይ  ሲሆን  የእስልምና አክራሪ ታጣቂ ቡድኑ   ከፍተኛ አመራርን  ሊላማ ያደረገ መሆኑ ተገልጿል  ።

እስካሁን ድረስ  በአየር ድብደባው ምክንያት  ምን  ያህል  ጉዳት  እንደደረሰ ያልታወቀ መሆኑንና አስፈላጊ ከሆነ  በአየር ጥቃቱ የደረሰው ጉዳት እንደታወቀ   ተጨማሪ መረጃ ሊሠጥ እንደሚችል  አድሚራ ኬርባይ ተናግረዋል ።   

በሶማሊያ አልሻባብ ቡድን ላይ የተፈጸመው  የአየር ጥቃት በሰው አልባ አውሮፕላኖች የተካሄደ  መሆኑን  የፔንታጎን ኃላፊው አመልክተዋል ።

ባለፈው ቅዳሜ ሁለት የሶማሊያ የጦር አዛዦች የአልሻባብ ከፍተኛ አመራሮችንም  መያዛቸውን መናገራቸው የሚታወስ  ሲሆን  የአልሻባብ  የደህንነት ዋና አዛዥ  ዘካሪያ እስማኤል አህመድ ሀርሲ  በኢል ዋክ ከተማ አቅራቢያ በቁጥጥር ሥር  መዋላቸው  ተገልጿል ።  

የአልሻባብ  ታጣቂ ቡድን ባለፈው ሳምንት  ሞቃዲሾ በሚገኘው  የአፍሪካ ህብረት ሰላም አስካባሪ ኃይል ወታደራዊ ይዞታ ላይ ጥቃት በመፈጸም የኡጋንዳ ወታደ ችና ሲቪሎች  እንዲገደሉ ካደረገ  በኋላ  የቡድኑ ወሳኝ  አመራሮች እየታደኑ ይገኛሉ ።

አልሻባብ በበኩሉ  በሞቃዲሾ  የአፍሪካ  ህብረት ይዞታ ላይ  የፈጸመው ጥቃት  ዩናይትድ ስቴትስ  የቀድሞ የቡድኑ መሪ በሆነው ጎዳኔ ላይ   ለፈጸመችው  ግድያ  የበቀል ምላሽ  እንደሚሆን  ገልጿል ።

የዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ  የቀድሞ  የአልሻባብ መሪ ጎዳኔ ያለበት ቦታ ለጠቆመ ግለሰብ   የ7 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ሽልማት መሥጠቱ ይታወሳል ። ( ምንጭ : ሲኤን ኤን )

(ትርጉም :  በሰለሞን ተስፋዬ)