የጋምቢያው ፕረዚዳንት የነበሩት ያህያ ጃሜህ ወደ ጊኒ ሸሹ

ከወራት በፊት በምርጫ በተቀናቃኛቸው ባሮው የተሸነፉት ያህያ ጃሜህ ሀገር ለቀው ወደ ጊኒ መሸሻቸው ተገለጸ  ፡፡

ጋምቢያን ለ22 ዓመታት የመሩት ጃሜህ ከአገር ሲወጡ መዳረሻቸውን ጊኒ ቢያደርጉም በቋሚነት ወደ ኢኳቶሪያል ጊኒ እንደሚያቀኑ ነው የተመለከተው ፡፡

ጃሜህ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ በርካታ የሀገሪቱ ባለስልጣናትና ደጋፊዎቻቸው ተገኝተው አሸኛኘት አድርገውላቸዋል፡፡

ደጋፊዎቻቸው በአውሮፕላን ማረፊያ ተገኝተው እያለቀሱ ሲሸኟቸው አብዛኛዎቹ ጋመቢያዊያን ደስታቸውን በመግለጽ ላይ መሆናቸው ተዘግቧል፡፡

ባለፈው ታህሳስ በተደረገ ምርጫ አዳማ ባሮ ማሸነፋቸውን ተከትሎ ጃሜህ ስልጣን እለቃለሁ ካሉ በኋላ ምርጫው ችግር ነበረበት በሚል ስልጣን እንደማይለቁ መናገራቸው በአገሪቱ አለመረጋጋት ፈጥሮ መቆየቱን ነው የተጠቀሰው ፡፡

ይህንን ተከትሎ ተመራጩ ፕሬዝዳንት ባሮው በዓለ ሲመታቸውን በስደት በሚገኙበት በሴኔጋል የጋምቢያ ኤምባሲ  መፈጸማቸው ይታወቃል ፡፡

የምዕራብ አፍሪካ ሀገራት ወታደራዊ ዘመቻ ለማድረግ መዘጋጀት የራሱ ተጽእኖ መፍጠሩንም ተመልክቷል ፡፡

ጃሜህ ከስልጣን ለመውረድ የተስማሙበት መንገድ ገልጽ ያለመሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ

የአዲሱ የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት አዳማ ባሮው አማካሪ ማይ አህማድ ፋቲ እንዳስታወቁት ፤ ጃሜህ ከሀገር ሲወጡ እጅግ ውድ ተሽከርካሪዎች እና ሌሎች እቃዎች በቻድ የጭነት አውሮፕላን በመጫን ወስደዋል ።

ያህያ ጃሜህ ባለፉት ሁለት ሳምንታት 11 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር መውሰዳቸውንም አመልክተዋል፡፡

የጋምቢያ ካዝና ባዶ መሆኑን በሀገሪቱ የፋይናንስ ሚኒስቴር እና በጋምቢያ ማዕከላዊ ባንክ መረጋጡን ጨምረው አስታውቀዋል ፡፡

አዲሱ ተመራጭ ወደ ጋምቢያ ለመግባት በጉጉት እየጠበቁ ቢሆንም የአገሪቱ ጸጥታ አደገኛ መሆኑን ነው እየተገለጸ የሚገኘው -(ቢቢሲ) ፡፡