የጊኒ ፕሬዚዳንት አልፋ ኮንዴ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር  ሆነው ተመረጡ

የጊኒ ሪፐብሊክ  ፕሬዚደንት የሆኑት  አልፋ ኮንዴ  እኤአ በ 2017   የአፍሪካ  ህብረት  የመሪዎች  ሊቀመንበር  ሆነው  ተመረጡ  ።

ዛሬ  በተካሄደው  28ኛው  የአፍሪካ  ህብረት የመሪዎች ስብሰባ  የተለያዩ  ክቡራን እንግዶች   በተገኙበት  በተከናወነው  ምርጫ  የምዕራብ አፍሪካ  ተወካይ የሆኑት  አልፋ ኮንዴ ድምጽ በማግኘታቸው  ከአምናው  የአፍሪካ ህብረት መሪዎች ሊቀመንበር ከሆኑት  የቻድ ፕሬዚደንት  ኢድሪስ  ዴቢ ሥልጣናቸውን ተረክበዋል ።  

ተመራጩ ሊቀመንበር  ፕሬዚደንት አልፋ ኮንዴ “ አፍሪካ  በተባበሩት መንግሥታት የተለያዩ ድርጅቶች ያላትን አነስተኛ የተወካይነት መቀመጫ ለማሳደግ እንደሚሠሩና የአፍሪካን  ድምጽ እንዲሰማ ጥረት እንደሚያደርጉ ” አስታውቀዋል ።

እንደ አልፋ ኮንዴ ገለጻ  አፍሪካ በአንድ ድምጽ የምትናገርና በምንም  መልኩ ቢሆን  የማትከፋፈል መሆኗንና   በአፍሪካ አገራት  መካከል  ይበልጥ ትብብርን ለማጉልበት ይሠራሉ ።

አፍሪካ  የተጋረጠባትን የወጣቶች ሥራ አጥነት ፣ የህገ ወጥ የሰዎች ዝውውርና  የኃይል ልማትን  ለማጠናከር  በሥልጣን ዘመናቸው ተገቢ የልማት ሥራዎችን ማከናወን  እንደሚንቀሳቀሱ  ገልጸዋል ።       

የተለያዩ የሃይል  ምንጮች  በማስፋፋት ሥራዎች ላይ በማተኮር  የሃይል አቅርቦት እጥረት  ያለባቸውን  700 ሚሊዮን  አፍሪካውያንን  ለመደገፍ   እንደሚተጉ  አረጋግጠዋል፡፡

ፕሬዚደንት አልፋ ኮንዴ ወጣቶችን  ብዛት  ማዕከል  ያደረጉ  የልማት ሥራዎችን  በአህጉሪቱ  እንዲካሄዱ ለማድረግ ግፊት ለማሳደር  ማቀዳቸውን አስረድተዋል ።  

የተሰናባቹ  የአፍሪካ ህብረት  ሊቀመንበር  ፕሬዚደንት  ኢድሪስ  በበኩላቸው በአፍሪካ ሰላምና መረጋጋትን ለማምጣት ተገቢውን ሚና እንደተጫወቱና   የተቋማትን በለውጥ ሂደት እንዲያልፉ የማድረግ ሥራዎችን ማከናወናቸውን አስገንዝበዋል ።

28ኛው የአፍሪካ  የመሪዎች  ስብሰባ  በነገው ዕለት  ቀጣዩን የአፍሪካ  መሪዎች ሊቀመንበር  እንደሚመርጥ ዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል  ዘግቧል  ።

(ትርጉም- በሰለሞን ተስፋዬ)