የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ የተለያዩ ውሳኔዎችን በማሳለፍ ተጠናቀቀ

በአዲስ አበባ  ለሳምንት ያህል ሲካሄድ የቆየው 28ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች  ጉባኤ  በተለያዩ ዘርፎች የህብረቱ ኮሚሽነሮችን  በመምረጥ ተጠናቋል ።  

በጉባኤው ላይ የስንብት ንግግር ያደረጉት የቀድሞ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽነር ዶክተር ድላሚኒ ዙማ  ቀጣዩ  የአፍሪካ  ህብረት  ኮሚሽነር  ሙሳ ማህማት የአፍሪካን የአንድነት ተልዕኮና የተቀመጡ ግቦችን  እንዲያሳኩ  ጥሪ አቅርበዋል ።  

አዲሱ  አፍሪካ ህብረት ኮሚሽነር በህብረቱ የተጣለውን መሠረት ይበልጥ የማጠናከር ሥራ እንደሚያከናውናሉ  ብለውን እንደሚጠብቁ  የገለጹት  ዶክተር ድላሚኒ ዙማ አ.ኤ.አ በአፍሪካ  በጠመንጃ የሚካሄድ  ተኩስን ሙሉ ለሙሉ ማስቆምና  ሰላማዊና የበለጸገች አፍሪካን እውን ማድረግ   የህብረቱ ዋነኛ ራዕይ መሆኑን አስገንዝበዋል ።

በተጨማሪም “  የአፍሪካውያን ድምጽ  በዓለም የሚያስተጋባ  ለማድረግ  ከመቼውም በላይ አፍሪካውያን በማንም ሳይከፋፈሉ  በአንድነት መንቀሳቀስ  ይገባናል ”  ብለዋል ።

አዲሱ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽነር  ሙሳ ማህመት በበኩላቸው የተለያዩ እንቅፋቶችን  እያጋጠሙም ቢሆን የአፍሪካ ህዝብን  በሙሉ  ሃላፊነት ለማገልገል   መዘጋጀታቸውን አረጋግጠዋል ።             

እንደ ማህመት ገለጻ “  አፍሪካን   ብዝሃነቷን  ማዕከል  በማድረግ ማገልገል  ቀላል የማይባል  ቢሆንም  ፈተናዎቹን መጋፈጥ አያስፈራኝም   የአፍሪካን   ራዕይ የማሳካው   ከሌሎች  ጋር በመተባባር ነው   ”  አስረድተዋል ።

የ2063   የልማት  ግቦችን  ለማሳካት  የአፍሪካውያን  ወጣቶች ፣ ምሁራንና የግል ዘርፉ  ተሳትፎ እጅግ መዋኝ መሆኑንም  ማህመት አስምረውበታል ።  

( ትርጉም : በሰለሞን ተስፋዬ )