የዓለማችን ሀገራት እዳ የመሸከም አቅምን በመመርምር የሚታወቀው እስታንዳደር ኤንድ ፑርስ የተባለው የአሜሪካ የፋይናንስ አገልግሎት ምርመራ ተቋም የደቡብ አፍሪካን ከአለም የፋይናንስ ገበያ የመበደር አቅም ጤናማ እንዳልሆነ አስታወቀ፡፡
ተቋሙ የገሪቷን የመበደር አቅም ጤናማ አይደለም ለማለት የበቃው የአገሪቷ ፕሬዜዳነት ጃኮብ ዙማ የገንዘብ ሚኒስትራቸውን ጨምሮ 12 የካቢኔ ሚኒስትሮቻቸውን ባልተጠበቀ ሁኔታ ካባረሩ በኋላ ነው ፡፡
የፕሬዝዳንቱ ያልተጠበቀ የካቢኔ ሹም ሽር ለአፍሪካ ልዕለ ሃያል ኢኮኖሚ ያልተጠበቀ አደጋን ጋርጧል፡፡
እንደተቋሙ ገለፃ ከሆነ የአገሪቷ የመበደር አቅም ጤናማ አይደለም መባሉ የአገሪቷን የመበደር አቅም ከመጉዳቱ በተጨማሪ የሃገሪቷን የእድገት ህልም እንዳታሳካ ያደርጋል፡፡
ተቋሙ ደቡብ አፍሪካ ከአለም የገንዘብ ገበያ ከጤናማነት ወደ ህመምተኝነት ሲያንሸራትታት አገሪቷ ከአለምአቀፍ የገንዘብ ተቋማት ለመበደር ያላትን እድል ባያሳጣም ከፍተኛ ወለድ እንድትከፍል ግን ያስገድዳታል፡፡
ከዚህ በተጨማሪ በአገሪቷ መዋእለንዋያቸውን ለማፍሰስ ፍቃደኛ የሆኑ ባለሀብቶች ሊከሰት በሚችለው የፖለቲካ አለመረጋጋት ምክንያት ሀብታቸውን ከማፍሰሳቸው በፊት ሁለቴ እንዲያስቡ ያደርጋቸዋል፡፡
ይህ በድምሩ ሲታይ ሀገሪቷ የወጠነቻቸውን የእድገት እቅዶች እንዳይሳኩ ያደርጋል ማለት ነው ፡፡
የደቡብ አፍሪካ ብሄራዊ የመገባያያ ገንዘብ የሆነው ራንድ ከዶላር ጋር ያለው ምጣኔ ካለፈው አርብ ጀም የመግዛት አቅሙ 3 በመቶ ቀንሷል፡፡
እስታንዳደር ኤንድ ፑርስ በሪፖርቱ እንደተነበየው ከሆነ ፕሬዝዳንቱ የወሰዱት እርምጃ በሀገሪቷ የፖለቲካ አለመረጋጋትን ከማስከተሉ በተጨማሪ የፖሊሲ ለውጥ ሊያስከትል ይችላል፡፡
የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳትን ጃኮብ ዙማ በወሰዱት እርምጃ ከሚመሩት ፓርቲያቸው ተቋውሞ የገጠማቸው ሲሆን የሀገሪቱ ዋና ዋና የፖለቲካ ጠቃዋሚ ፓርቲዎችም እንዲሁ ተቋውሟቸውን በመግልጽ ላይ ናቸው፡፡
ፕሬዝዳንቱ በሞያቸው ክብርና ሞገስን የተላበሱትን የገንዘብ ሚኒስትራቸውን እምብዛም ስልሀገሪቱ የገንዘብ ስርአት በቂ እውቀት እንደሌላቸው በሚነገርላቸው የሃገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትራቸው ተክተዋቸዋል፡፡
ከዚህ ቀደም በተመሳሳይ መልኩ ፕሬዝንዳቱ የገንዘብ ሚኒስትሩን ከስልጣናቸው ካነሷቸው በኋላ መልሰው መሾማቸው ይታወሳል፡፡
400 መቀመጫ ባለው የደቡብ አፍሪካ ህግ አውጪ ምክር ቤት ውስጥ የፕሬዝዳንቱ ፓርቲ የአፍሪካ ናሽናል ኮንግረስ 249 መቀመጫቸውን በመያዙ ሓገሪቷን በማስተዳደር ላይ ይገኛል፡
ፕሬዝዳንት ጃኮብ ዙማ በመንግስት አስተዳደራቸው የስነ -ምግባር ጉድለት የተነሳ ተቃዎሞን ማስተናገድ ከጀመሩ ውለው አድረዋል፡፡