በሰማሊያ የታችኛው ሸበሌ አካባቢ በመንገድ ዳር የተጠመደ ቦምብ ፈንድቶ በአነስተኛ የህዝብ ተሸከርካሪ ውስጥ የነበሩ ከ19 የማያንሱ ሰዎች መሞታቸውን አንድ የሀገሪቱ የፀጥታ ባለስልጣን አስታውቀዋል፡፡
በፍንዳታው ከሟቾች በተጨማሪ ስድስት ሰዎች መቁሰላቸውን ነው የአካባቢው የፀጥታ ሃላፊ ኑር አብዱላሂ የገለጹት ፡፡
ተሸከርካሪው በሚሄድበት መንገድ ዳር በርካታ ቦምቦች ተቀብረው እንደነበርና ከዚያ ውስጥ የተወሰነው ፈንድቶ ነው ጉዳቱ የደረሰው ብለዋል፡፡
ጉዳቱ እጅግ አሳዛኝ ሲሆን ተሸከርካሪው በመጋየቱ የተወሰኑት ሰዎች እሳቱ እንዳቃጠላቸው ገልጸዋል፡፡
ለጥቃቱ ሃላፊነት አስካሁን የወሰደ ቡድን የለም-(ኤፍ ቢ ሲ)፡፡