ግብጽ ከሽብር ጥቃት በኋላ የ3 ወር የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አወጀች

የግብጹ ፕሬዚዳንት አብዱል ፈታህ አልሲሲ ትናንት በሁለት የግብጽ የኮፕቲክ ቤተክርስቲያናት ላይ  የደረሰውን የሽብር ጥቃት  ተከትሎ  የሶስት ወር  የአስቸኳይ  ጊዜ አወጀች ።

በትናንትናው  ዕለት በሁለት የኮፕቲክ ቤተክርስቲያናት ላይ በደረሰው የሽብርተኞች ጥቃት  44 የሚሆኑ ሰዎች  የተገደሉ ሲሆን  ለሶስት ወራት የሚቆይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲወጣ ተደርጓል ።

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ተግባራዊ ከመሆኑ በፊት በፓርላማው መፅደቅ እንደሚገባው የተመለከተ  ሲሆን  በአዋጁ  መሠረት የመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች ከሽብሩ ጋር ግንኙነት ያላቸው አካላትን ያለምንም  የእሥር ማዘዣ በቁጥጥር ሥር የማዋልና  መኖሪያ ቤታቸውን መበርበር ያስችላል ።

የኢስላሚክ እስቴት ( አይኤስ) በግብጽ ታንታና አሌክዛንዴሪያ ከደረሰው የሽብር ጥቃት ጀርባ እጁ  እንዳለበት ገልጿል ።

አይኤስ በቅርቡ  በግብጽ በሚገኙ ኮፕሊኮችን ዒላማ ያደረገ  በርካታ የሽብር ጥቃት ለማድረስ  ዛቻ  ሲያቀርብ መቆየቱ ይታወሳል ።

ፕሬዚደንት አልሲሲ  በቤተ መንግሥት  ከብሔራዊ የመከላከያ ምክር ቤት ጋር በመሆን  በሽብር ጥቃቱን አስመልክቶ ባደረጉት  ስብሰባ  አጽዕኖት ሠጥተው እንደተናገሩት “ ከአክራሪዎችና ረጅምና መራራ ትግል እናደርጋለን ” ብለዋል ።   ሁሉም  ህገመንግሥታዊ መርሆችና የህግ አግባብ አሠራሮች በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲተኩ ይደረጋል ብለዋል ።

የግብጽ  አብዛኛው  የግብጽ ፓርላማ  አባላት  ፕሬዚደንት አልሲሲን እንደሚደግፉ አመልክተዋል ።

አልሲሲ  የብሔራዊ  የመከላከያ ምክር ቤቱን ለስብሰባ  ከመጥራታቸው በፊት   የግብጽ ሠራዊት በአገሪቱ የሚገኙ  ዋና ዋና መሠረት ልማቶችን  ከጥቃት  እንዲከላከል  ትዕዛዝ ተላልፎለታል ።

 የሽብር ጥቃቱ  እየሱስ ክርስቶስ ወደ እየሩሳሌም የገባበት ቀን እንደሆነና በክርስቲያኖች ዘንድ እንደ  ቅዱስ  ቀን ተብሎ  በሚታመንበት  ዕለት ጋር እንዲገጣጠም ተደርጎ የተፈጸመ ጥቃት መሆኑ ተገልጿል ።  

አይኤስ  በመግለጫው  ሁለት አጥፍቶ ጠፊዎች  የሽብር ጥቃቱን  መፈጸማቸውን  ተናግሯል ።

 በሰሜናዊ  ታንታ ከተማ  የሚገኘውን የቅዱስ ጊዮርጊስ  ቤተ ክርስቲያንን  ዒላማ  በማድረግ  በተፈጸመው   የመጀመሪያው የፊንጅ  ጥቃት 27  ሰዎች መገደላቸውንና በርካታ ፖሊሶች ላይ የመቁሰል አደጋ እንደደረሰባቸው  የግብጽ  የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል ።

 ከሰዓታት  በኋላ  በአሌግዛንዴሪያ ከተማ በሚገኘው ቅዱስ ማርቆስ ቤተክርስቲያን  በፖሊስ እንዳይገባ የተከለከለው  የሁለተኛው ጥቃት ፈጻሚ  ከቤተክርስቲያኑ  ግቢ ውጪ  በወረወረው ፈንጅ 17 ሰዎች ተገድለዋል እንዲሁም ቁጠራቸው ባለታወቀ ፖሊሲዎች ቆስለዋል ።   

የአክራሪው አይኤስ በመግለጫው   “  መናፍቃንና የመናፍቃን ተከታዮች  በእኛና በእነሱ መካከል ሰፊ ልዩነት አለ  ስለዚህም ቅጣቱን  በልጆቻቸው  ደም ይከፍላሉ ” ማለታቸውን  ሮይተርስ  የዜና ወኪል ዘግቧል ።   (ምንጭ  ቢቢሲ)