በደቡብ ሱዳን እና በሶማሊያ በሽታና ጾታዊ ጥቃት አሳሳቢ እየሆኑ መምጣታቸው ተገለጸ

በደቡብ ሱዳንና ሶማሊያ  የበሽታና ፆታዊ ጥቃቶች አሳሳቢ እየሆኑ መምጣታቸውን በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ከተለያዩ ዘርፎች የተውጣጡ የሥራ ኃላፊዎች ገለጹ ።

የተባባሩት መንግሥታት ድርጅት የሥራ ኃላፊዎች ሰሞኑን በደቡብ ሱዳንና  በሶማሊያ የተከሰተውን ጊዚያዊ ቀውስ በጎበኙበት ወቅት እንደገለጹት በሁለቱ አገራት ለረሃብርና ከጦርነት ቀውስ በተጨማሪ ከምግብና ከውሃ እጥረት ጋር ተያይዞ የበሽታዎች መስፋፋት በአሳሳቢ ደረጃ ላይ ይገኛል ።

ሁለቱም አገራት በህጻናትና ሴቶች ላይ ሳይቀር የሚፈጸሙት ፆታዊ ጥቃቶች  ቀውስ  እየፈጠሩ መምጣታቸውን  የሥራ ኃላፊዎቹ ታዝበዋል ።

የተባባሩት መንግስታት ድርጅት ኃላፊዎችን በመወከል በኒውዮርክ ለጋዜጠኞች መግለጫ የሰጡት ጆን ጊንግ በሶማሊያ ከ6.2 ሚሊየን በላይ ህዝብ ለረሀብ መጋለጡን ተከትሎ ለኮሌራና ኩፍኝ በሽታዎች ተጋላጭ ሆኗል ብለዋል፡፡

በደቡብ ሱዳን በኩል የረሀብ  ተጋላጮች  ቁጥር ወደ 7.5 ሚሊየን ከፍ ይላል፡፡ ከዚህ ውስጥ ግማሾቹ መኖሪቸውን ለቀው ተፈናቅለዋል ብለዋል ፡፡

 የድቡብ ሱዳኑን አስከፊ ያደረገው ደግሞ ፆታዊ ጥቃቱ የከፋ ደረጃ ላይ መድረሱ ነው ያሉት ጆን ጊንግ  ለአካለ መጠን ያልደረሱ ህፃናት እና አረጋውያን ሴቶች ሳይቀሩ ጥቃት ይደርስባቸዋል፡፡

በተጨማሪም  በደቡብ ሱዳን ባለፈው አመት የነበረው የኮሌራ በሽታ ስርጭት መጠን ዘንድሮ በ700 እጅ ጨምሯል ብለዋል ፡፡

የደቡብ ሱዳን ሌላው አስቸጋሪ ሁኔታ ለእርዳታ ሰራተኞች እጅግ አደገኛ ስፍራ መሆኗን የጠቀሱት ጆን ጊንግ  በቅርቡ በነበሩት ግጭቶች እንኳን 82 የሰብአዊ እርዳታ ሰራተኞች ህይወታቸውን ማጣታቸውን ተናግረዋል፡፡ ( ምንጭ : ሪሊፍ ዌብ)