ግብፅ እና ሱዳን የሽብር ዓላማን ያነገቡ የመንግስት ተቃዋሚ ኃይሎችን ላለመደገፍ ቃል ተገባቡ

ግብጽና ሱዳን  የሽብር ዓላማን ያነገቡ የሁለቱ አገራት መንግሥታት የተቃዋሚ ኃይሎችን ላለመደገፍ  ተስማሙ  ።

ሁለቱ አገራት ቀረቤታ ያላቸውና የአባይ ውሃ  ውሃ የሚያዛምዳቸው ጉረቤታሞች፤  የጋራ ድንበር እንዳላቸው አገራት  ጥምረታቸውና ግንኙነታቸው  የሚፈለገውን ያህል እንዳልሆነ ይገለጿል ፡፡

እኤአ በ1993 አሜሪካ ሱዳንን የሽብር ቀጣና ስትል ፈርጃ እንኳ ያልተለየቻት ግብፅ፤ ከሁለት ዓመት በኋላ ግን በሱዳን የሚገኘውን ሀያሌብ የተሰኘ የከፍታ ስፍራ ተቆጣጥራ በሱዳን እና ደቡብ ሱዳን አለመግባባት ወቅት የቀድሞ ወዳጇን ስትበቀል ነበር ተብሏል፡፡

ሱዳን እና ግብፅ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጣር በ2004 ጀምሮ የሁለቱ አገራት ዜጎች ያለ ቪዛ  ገደብ የሁለቱ አገራት ዜጎች እንዲገቡ የሚያስችል ስምምነት ላይ መድረሳቸው ደግሞ ጥሩ ግንኙነት  ምሳሌ  መሆኑ  በብዙዎች ተገምቶ ነበር ፡፡

ከስምምነት ከተደረሰ በኋላ  ዓመታት በኋላ ሱዳን የግብፅን የመረጃ አገልግሎት ተቋም በሱዳን የሚገኙ ፀረ-መንግስት  የሆኑ የሽብር ቡድኖችን ይደግፋል ስትል ወንጅላ  አቅርባ እንደነበር ይታወሳል ፡፡

የግብፅ የመገናኛ ብዙሃንም ካይሮ የሽብር ቡድን ብላ የፈረጀችውን የሙስሊም ወንድማማች ቡድን በ2013 የመፈንቅለ መንግስት ባደረገው ንቅናቄን ሱዳን ድጋፍ አድርጋለች በማለት  ሲ የሁለቱን አገራት መካከል ያለውን ግንኙነት ጥላቻ እንዳለው  አጉልተው ሲያሳዩ እንደበር ይነገራል፡፡

በአሁኑ ወቅት የሁለቱ አገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በካርቱም በነበራቸው ግንኙነት በሱዳን የሚገኙ ፀረ ሠላም ኃይሎችን ግብፅ ላለመደገፍ እና በግብፅ የሚገኙ የመንግሥት ተቃዋሚዎችን  ሱዳን ላለመደገፍ  ቃል ተግባብተዋል፡፡

የአሁኑ የሁለቱ  አገራት ስምምነት እንደቀድሞውም ሁሉ ወቅት አፈራሽ በማለት አስተያየታቸውን  የሚሠጡ እንዳሉም   ይገለጻል ፡፡

ባለፈው ወር እድሜያቸው ከ19-50 የሚሆኑ ግብፃውያን ብቻ ወደ ሱዳን ያለ ቪዛ መግባት ይችላሉ ስትል ካርቱም ያረቀቀችውን ግብፅ መቀበሏን ያስታወሱት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ኢብራሒም ጋንዱር ይህ የፖሊሲያችን ውጤት ነው፤ ከአሁን በኋላ ለሽብር ዓላማ ነፍጥ ያነገቡ ኃይሎችን አንደግፍም ሲሉ የግብፁ አቻቸው ሳሜህ ሽኩሪህ ደግሞ አገራቱ እጅ ለእጅ ተያይዘው መስራት አለባቸው ብለዋል፡፡ ( ምንጭ : አረብ ኒውስ)