33ኛው የምስራቅ ናይል የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል

ሰኔ 08/2013 (ዋልታ) – 33ኛው የምስራቅ ናይል የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል።

በውይይቱ ላይ የኢፌዴሪ የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጅነር ስለሺ በቀለ፣ የደቡብ ሱዳኑ የውሃ ሚኒስትር ማናዋ ፒተር ጋትኩታ እንዲሁም የሱዳን የውሃ ሚኒስትር ያሲር አባስ ተገኝተዋል።

በስብሰባው የናይል ተፋሰስን በጋራ ማልማት የሚቻልበት መንገድና እስካሁን በተፋሰሱ  የተሰሩ ስራዎች የሚቃኙ ይሆናል።

ለአንድ ቀን በሚካሄደው ውይይት የናይል ቤዚን ኢንሺየቲቭ እንዲሁም የቴክኒክ ባለሙያዎች በውይይቱ ላይ ታድመዋል።

ግብጽ የዚህ ምክር ቤቱ አባል ብትሆንም በስብሰባው ሳትገኝ መቅረቷን ከውሃ ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

በአውሮፓዊያኑ 2019 ተመሳሳይ የምክክር መድረክ መካሄዱ ይታወሳል።