የቻይና-አፍሪካ የንግድ ግንኙነት ተጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል ተባለ

ቻይና ከአፍሪካ ጋር ያላትን የንግድ ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከር እንደምትፈልግ በፕሬዝዳንቷ በኩል አስታውቃለች።  

ቻይና የንግድ ትስስር እያስፋፉና እያጠናከሩ ካሉ  የአለም ሀገራት በቀዳሚነት ትጠቀሳለች።ይህም የኢኮኖሚ አቅሟ እንዲጨምርና ከአሜሪካን በመቀጠል የንግድ ኢንዱስትሪውን እንድትመራ አስችሏታል።ለዚህም በቤልጅንግ እየተካሄደ ያለው የቻይና አፍሪካ የትብብር ፎረም ዋነኛ ማሳይ ነው።

በቤልጅንግ እየተካሄደ ባለው የቻይና አፍሪካ  የትብብር  ፎረም  የንግድ ግንኙነቱ  የስራ እድልን ከመፍጠርን የሀገር ውስጥ ምርትን ከማሳደግ አንፃር ከፍተኛ መሆኑ ተገልጿል።

የኣይናው ፕሬዝዳንት ሺ ዚምቢንግ እንደገለፁት ቻይናና አፍሪካ ሁለቱም በጋራ የማደግ ፍላጎት አላቸው ስለሆነም  ቻይና ከአፍሪካ  ጋር ያላትን የንግድ ትስስር ይበልጥ ማጠናከር ትፈልጋለች ፣የአፍሪካ  ስራ ፈጣሪዎች  ወደ  ቻይና ለመምጣት ፍላጎቱ ካላቸው በደስታ እንደሚቀበሏቸውና የቻይና ባለሃብቶች አፍሪካ ሄደው መዋዕለ ነዋያቸውን እንዲያፈሱ ቤልጂንግ ታበረታታለች ብለዋል።

በቤልጅንግ እየተካሄደ ባለው የቻይና አፍሪካ  የትብብር  ፎረም  ቻይና ከአፍሪካ ጋር በአረንጓዴ ልማት፡በግብርናው ዘርፍ፡በጤና እንዲሁም ሰላምና ፀጥታን ጨምሮ በስምንት መስኮች በጋራ መስራት እንደምትፈልግ አስታውቃለች።

ቻይናውያን ባለሃብቶች በአፍሪካ ትላልቅ የልማት ዘርፎች  በተለይ በመንገድ በባቡር ግንባታውና የኤለክትሪክ ማመንጫ ፕሮጀክቶች እየተሳተፉ እንደሚገኙ ይታወቃል።

የቻይና አፍሪካ የንግድ ግንኙነት በከፍተኛ ደረጃ እያደገ መጥቷል። በተለይ ደቡበ አፍሪካ፡አንጎላና ናይጀሪያ የአንበሳውን ድርሻ ሲይዙ  እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር የቻይና አፍሪካ የንግድ ግንኙነት  በ1978 ከነበረው 765 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር 2017 ወደ170 ቢሊዮን የአሜሪላን ዶላር አድጓል።

ይህ የቻይና አፍሪካ የንግድ ግንኙነት ለሀገራቱ በጋራ የማደግ ህልምና በተለይ ደግሞ በአፍሪካ ውስጥ ያሉ የስራ ፈጣሪዎችን በማበረታታት የተሸለ እምርታ ያመጣል ተብሎ ተስፋ ተጥሎበታል።(ምንጭ: ሲጂቲኤን)