የኤርትራና ጅቡቲ ፕሬዝዳንቶች በሳውዲ አረቢያ መሪ ፍት ለፊት ተወያዩ

የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂና የጅቡቲው ፕሬዚዳንት አስማኤል ኦማር ጊሌ በሳዑዲ አረቢያ ፊት ለፊት ተገናኝተው ተወያይተዋል።

ለዓመታት በድንበር ግጭት ምክንያት ግንኙነታቸውን አቋርጠው የኖሩት ሁለቱ ሀገራት ግንኙነታቸውን ለመጀመር ተስማምተዋል።

ትናንትናም በመሪዎች ደረጃ ፊት ለፊት ተገናኝተው በመወያየት ግንኙነታቸውን የማደሱን ስራ በይፋ ጀምረዋል።

በቅርቡ የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ ከኤርትራና ሶማሊያ አቻቸው ጋር በመሆኑን በጅቡቲ ጉብኝት በማድረግ የሀገራቱን ግንኙነት ዳግም ለማስጀመር ዲፕሎማሲያዊ ጥረት መጀመራቸው አይዘነጋም።

በትናንቱም በፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂና እና ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ኦማር ጌሌ ውይይት ላይም በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮቹ ጉብኝት ወቅት በተቀመጠው መርህ መሰረት ግንኙነታቸውን ለማደስ ስምምነት ላይ ተደርሷል።