ፕሬዝዳንት አልበሺር ፖሊስ በሰልፈኞች ላይ የሚወስደውን እርምጃ ተመጣጣኝ እንዲያደርግ ትዕዛዝ አስተላለፉ

የሱዳኑ ፕሬዝዳንት ኦማር ሀሰን አልበሺር ፖሊስ በመንግስት ቃቋውሞ በወጡ ሰልፈኞች ላይ የሚወስደውን እርምጃ ገታ እንዲያደርግ ትዕዛዝ አስተላልፈዋል፡፡

ፕሬዝዳንቱ ትዕዛዙን ያስተላለፉት የመንግስታቱ ድርጅት ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጉቴርየስ የሱዳን መንግስት በሰልፈኞች ላይ ግድያ መፈጸሙን እንዲያቆም ማስጠንቀቃቸውን ተከትሎ ነው፡፡

ትላንት ከፖሊሶች ጋር በነበራቸው ስብሰባም ተመጣጣኝ እርምጃ እንዲወሰድና ወደ ቀድሞ መረጋጋት ለመመለስ ውሳኔው መከበር እንዳለበት አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

አስራ ሁለት ቀናት ያስቆጠረው ህዝባዊ ተቃውሞው 19 ሰዎች መሞታቸው በመንግስት በኩል  የተነገረ ሲሆን አሚኔስቲ ኢንተራሽናል እስካሁን ባለው ቁጥሩን 37 አድርሶታል፡፡

የተቃውሞ ሰልፉ በገሪቱ የተከሰተውን የነዳጅ አቅርቦት እጥረትና የዳቦ ዋጋ መናር አስታኮ የተጀመረ ቢሆንም ከፈረንጆቹ 1989 አንስቶ የፕሬዝዳንትነት መንበሩን የተቆጣጠሩት አልበሺር ባፋጣኝ ከስልጣን ይውረዱ ወደሚል ጥያቄ አምርቷል፡፡

የህዝብ ማዕበሉን የተቀላቀሉት የህክምና ዶከተሮችም ዜጎች ፖሊስ ያልተመጣጠነ እርምጃ ባለመወሰዱ የከፋ ጉዳት እንደደረሰባቸው በማስተጋባት ላይ ናቸው፡፡

በ2017 አሜሪካ በሱዳን ላይ ለ20 አመታት ጥላው የነበረውን ማዕቀብ ማንሳቷን ተከትሎ ካርቱም ለከፍተኛ የውጪ ምንዛሪ እጥረትና ለዋጋ ግሽበት ተዳርጋለች፡፡

ተጽኖውም ዜጎች ምሬታቸውን  በአደባባይ ለማሰማት እንዲወጡ እገድዷቸዋል፡፡

አሁን ላይ ተቃውሞው ወደ ነውጥ ተለውጦ ወደ ዝርፊያ የተቀየረ ሲሆን የመንግስት ተቋማትን አውድሟል፤ሂዎትም ቀጥፏል፡፡

በእርግጥም ምጣኔ ሀብታዊ ችግሮች አሉብን ነገር ግን በዚህ መልኩ መፈታት አይችልም ሲሉም አልበሺር ተደምጠዋል፡፡

የአረቡ አለም ሀገራት እጣ እንዳይደርሰን እሰከማለትና ዜጎቻችን የስደት ሰለባ እንዲሆኑ መፍቀድ የለብንም ሲሉ ተማጽነዋል፡፡

መንግስት ተቋውሞን ከኑሮ ውድነት ጋር ለማስታከክ ቢሞክርም ተንታኞች እንደሚሉት ደግሞ የጎዳና ላይ ነውጡ ፖለቲካዊ ጫናንና የአልበሺርን ፖሊሲ በይፋ እስከ ማብጥልጠል የደረሰ ነው ይሉታል፡፡

ይህ ደግሞ አልበሺር ለ29 አመታት በብቸኝነት የተቆጣጠሩት የስልጣን መንበር ለውጥ ያሥፈልገዋል በሚሉ ተቃዋውሞዎች እንዲስተጋቡ በር ከፍቷል፡፡

በሱዳን አሁን እየሆነ ያለውን ክስተት ተከትሎም የተመድ ዋና ጻፊ አንቶኒዮ ጉቴርየስ የሟቾች ጉዳይ እንዲጣራና ባለስልጣናቱም ሀሳብን በነጻ የመግለጽና የመሰብሰብ መብት እንዲያከብሩ አስጠንቅቀዋል፡፡ /አልጀዚራ/