አሜሪካ በዚምባብዌ ኤምባሲ ከፈተች

አሜሪካ በዚምባብዌ ርዕሰ-ከተማ ሀራሬ አዲስ ኤምባሲ መክፈቷ ተገለጸ፡፡

የኤምባሲው መከፈት የሁለቱን አገራት ዘላቂ ወዳጅነት ለማሳየት ያለመ መሆኑን የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ገልጿል።

የኤምባሲው ህንጻ የዚምባብዌን የኪነ ህንጻ ጥበብ በማካተት ከአገር-በቀል ቁሳቁስ የተገነባ መሆኑ ተጠቅሷል።

በ300 ሚሊዮን ዶላር ወጪ የተገነባው ሕንፃ በአፍሪካ ትላልቅ ከሚባሉት የአሜሪካ ኤምባሲዎች አንዱ መሆኑም ተጠቁሟል።

(ምንጭ፡- ቢቢሲ)