በደቡብ አፍሪካ ጠቅላላ ምርጫ ተካሄደ

በደቡብ አፍሪካ ከ26 ሚሊየን በላይ ዜጎች በ22 ሺህ 925 የምርጫ ጣቢያዎች ድምጽ የሰጡበት ጠቅላላ ምርጫ ድምጽ ሰጥተዋል፡፡

በምርጫው በፓርላማው የተሻለ መቀመጫ የሚያገኘው ፓርቲ ፕሬዚዳንቱን ይመርጣል።

ገዥው አፍሪካን ናሽናል ኮንግረስ፣ ኢኮኖሚክ ፍሪደም ፋይተርስ እና የዴሞክራቲክ አሊያንስ ፓርቲዎች በምርጫው ዋነኛ ተፎካካሪዎች ናቸው።

ቅድመ ትንበያዎችም ገዥው ፓርቲ ዳግም ሃገሪቱን የመምራት እድል እንዳለው እያመላከቱ ነው፤ ይሁን እንጅ የቀድሞው የሃገሪቱን መሪ ጃኮብ ዙማ የሙስና ክስ ተከትሎ ፓርቲው ተቀባይነቱ እየወረደ ስለመምጣቱም ይነገራል።

በምርጫው አሸናፊ የሚሆነው ፓርቲ በመጪው ቅዳሜ ይፋ ይሆናል።

(ምንጭ፦ አልጀዚራ)