የደቡብ አፍሪካውን ምርጫ ኤ.ኤን.ሲ ፓርቲ እየመራ ነው

በደቡብ አፍሪካ አጠቃላይ ምርጫ ከተቆጠረው 50 በመቶ ያህል ድምጽ ገዥው ፓርቲ የአፍሪካ ብሄራዊ ኮንግረስ (ኤ.ኤን.ሲ) ፓርቲ በ57 በመቶ ድርሻን በመያዝ እየመራ ነው።

የሀገሪቱ ምርጫ ኮሚሽን ባወጣው መረጃ መሰረት ማዕከላዊ ዴሞክራሲያዊ ኅብረት (ዲ.ኤ) 23 ከመቶ፣ ግራ ዘመሙ የኢኮኖሚ ነፃነት አውጪ ፓርቲ (ኢ.ኤፍ.ኤፍ) 10 ከመቶ ድምፅ አግኝተዋል ነው የተባለው።

የምርጫው የመጨረሻ ውጤት በመጪው ቅዳሜ ይፋ ይደረጋል ተብሏል፡፡

የአሁኑ የኤ.ኤን.ሲ የምርጫ ውጤት 65 በመቶ ድረስ ከፍ ሊል እንደሚችል ተገምቷል፡፡

ይህም ሆኖ የገዥው የአፍሪካ ብሄራዊ ኮንግረስ ፓርቲ ከዚህ በፊት ከነበረው ውጤት በ8 በመቶ ቅናሽ ማሳየቱ ተገልጿል፡፡

በአውሮፓዊያኑ 2014 ኤ.ኤን.ሲ 73 ከመቶ ድምፅ ያገኘ ሲሆን በአሁኑ ጊዜ የፓርቲው ተቀባይነት በከፍተኛ ደረጃ እያሽቆለቆለ መምጣቱ ይነገራል።

(ምንጭ፡-አልጀዚራ)