ኦማር አልበሽር ላይ ክስ ተመሰረተባቸው

የቀድሞው የሱዳን ፕሬዚደንት ኦማር አልበሽር  ክስ ተመሰረተባቸው፡፡

ፕሬዚዳንቱ የተከሰሱት የእርሳቸውን አስተዳደር በመቃወም አደባባይ በመውጣት ህይዎታቸው ካለፈ የሃገሩቱ ዜጎች ጋር የተያያዘ መሆኑ ተነግሯል።

አልበሽር በሰላማዊ ተቃዋሚዎች ላይ ጣልቃ በመግባት ለዜጎች ህልፈት ምክንያት ናቸው በሚል መከሰሳቸውን አቃቤ ህግ አስታውቋል።

የቀድሞ ፕሬዚደንቱ በሕገ ወጥ የገንዘብ ዝውውርና ሽብርተኛን በመደገፍ ወንጀል ምርመራ እየተደረገባቸው ነውም ተብሏል።

አልበሽር ከሥልጣን ከወረዱ በኋላ የት እንዳሉ ባይታወቅም በእስር ላይ እንደሚገኙ ተገልጿል።

ኦማር ሃሰን አልበሽር ሃገሪቷን ለ30 ዓመታት ያክል መርተዋታል።

ባለፈው ታኅሳስ ወር የሱዳን መንግሥት በዳቦ ላይ ሦስት እጥፍ የዋጋ ጭማሬ ማድረጉን ተከትሎ የተቀሰቀሰው አመፅ ሚያዚያ ወር ላይም በህዝባዊ ተቃውሞ ከስልጣን መዉረዳቸዉ ይታወሳል፡፡

(ምንጭ፡- ቢቢሲ)