በርካታ ቁጥር ያላቸው ኬኒያዊያን የአልሸባብ ታጣቂ እየሆኑ ናቸው ተባለ

በርካታ ቁጥር ያላቸው ኬኒያዊያን የአልሸባብ ታጣቂ እየሆኑ ስለመሆናቸው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ መብት ተሟጋች አስታወቀ፡፡

እነዚህ ኬኒያዊያን አሸባሪ ቡድኑን ሲቀላቀሉ ታጣቂ ከመሆንም በተጨማሪ በተለያዩ የስራ ሃላፊነት ቡድኑን እንደሚያገለግሉ ነው የተገለፀው፡፡

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ይፋ ባደረገው መረጃ በርካታ ቁጥር ያላቸው ኬንያውያን አሁን ቡድኑን እየተቀላቀሉ እንደሚገኙ ገልጿል፡፡

መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ኬንያ የአፍሪካ ህብረትን በመቀላቀል ቡድኑን ለመዋጋት ወደ ሶማለያ ወታደሮቿን ከላከች በኋላ ቡድኑ የበቀል እርምጃዎችን እየወሰደ ይገኛልም ተብሏል፡፡

በዛው ልክ ደግሞ በርካታ ኬንያውያን ቡድኑን እተቀላቀሉ በተለዩ የሙያ ዘርፍ እያገለገሉት ይገኛሉ፡፡

የወጣው መረጃ እንደሚያመልክተው በዋናነት በፊት ለፊት ውግያ፣ ቡድኑ የሚጠቀምባቸዉን መገልጊያ እቃዎች እና ምግም በመሸከም እና ሴቶች ደግሞ ሚስት በመሆን ያገለግላሉ፡፡

ምንም እንኳ ቡድኑ በተደጋጋሚ በኬንያዊያን ላይ ጥቃት ቢያደርስም ቡድኑን የሚቀላቀሉ ኬንያዊያን ተገደው እንደሆነም የመንግስታቱ ድርጅት መረጃ አመላክቷል፡፡

ከቡድኑ አምልጠው ወደ ቄያቸው የተመለሱ ኬንያውያንን መረጃ ዋቢ በማድረግ አልጄዚራ እንደዘገበው መንግስት ለዜጎች ዋስትና ባለመስጠቱ ቡድኑ በተደጋጋሚ ወደ ኬንያ በመግባት ዜጎችን አፍኖ እንደሚወስድ ነው የገለፁት፡፡

ከዚህም በተጨማሪ ድህነት እና ተስፋ መቁረጥ ቡድኑን እንዲቀላቀሉ እንደሚያደርጋቸው ይገልፃሉ፡፡

የኬንያ መንግስት በዚህ ዙርያ የሰጠው ነገር ባይኖርም ኬንያ አልሸባብን በተመለከተ ያላትን አቋም የማትቀይር ስለመሆኗ አልጄዚራ ከባልስጣናት መረጃ አገኘሁ ሲል ዘግቧል፡፡

አልሸባብ በአለም አቀፍ የጥቁር መዝገብ ላይ የአልቃይዳ ክንፍ ሆኖ በምስራቅ እፍሪካ ምድር የሚርመሰመስ ቡድን ሆኖ መመዝገቡ የሚታወቅ ነው፡፡

አልሸባብ በኬንያ በተደጋጋሚ በሚያደርሳቸው ጥቃቶች ብርካታ ኬንያውያን ህይወታቸውን ለመገበር ተገደዋልም ነው የተባለው፡፡