የሱዳን የተቃዋሚ ፓርቲው ህብረት ከሽግግር ምክር ቤቱ ጋር ሲያደርግ በነበረው ድርድር አልተስማማም ተባለ

የሱዳን የተቃዋሚ ፓርቲው ህብረት ኤፍ ኤፍ ሲ ከህጋዊው የሽግግር ምክር ቤቱ ጋር ሲያደርግ በነበረው ድርድር ከስምምነት ሳደርሱ ቀርተዋል ተባለ፡፡

የሱዳኑ ወታደራዊ የሽግግር ካዉንስልና የለዉጥና ነፃነት ተቃዋሚ ሃይል ፓርቲ ለሁለተኛ ጊዜ ሲያደርጉት በነበረው ድርድር ስምምነት ላይ ሳይደርሱ በመቅረታቸው የጋራ ምክር ቤት ለመመስረት የተደረገው ጥረት ውድቅ ሆኗል፡፡

ሁለቱም ፓርቲዎች ህጋዊው ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ለመምረጥም ወጥነው እነደነበር ነው የተገለጸው፡፡

እሁድ በነበረው የምክር ቤቱ ዉሎ በባለሙያዎች የሚመራው የተቃዋሚዎች ህብረት ኤፍ ኤፍ ሲ ነጻ የምክር ቤቱ ፕረዚዳንት እንዲመረጥ ሃሳብ ቢያቀርብም በወታደራዊ ምክር ቤቱ ተቀባይነት ሳያገኝ ቀርቷል ተብሏል፡፡

በኤፍ ኤፍ ሲ ተቃዋሚ ህብረት እና በወታደራዊ ምክር ቤቱ መካከል የተፈጠረዉ ዉጥረት በዋናነት እያንዳንዱ ፓርቲ እኩል ተወካይ እንዲኖራቸዉ እና የሉአላዊ ምክር ቤቱ ሊቀመንበር ከየትኛዉ ወገን ይመረጥ የሚለዉ እንደሆነም ታዉቋል፡፡

በሁለቱም ወገኖች በኩል ምንም እንኳን አስካሁን ከስምምነት ላይ ባይደረስም በዉይይታቸዉ መጨረሻ ላይ ግን የሱዳናዉያንን ጥያቄ ለመመለስና የሱዳኑ ለዉጥ ግቡን እንዲመታ የማያዳግም ስምምነት ላይ ለመድረስ እንደሚሰሩ ቃል መገባቱንም ሱዳን ትሪቡን አስነብቧል፡፡

የአፍሪካ ህብረት የሰላም እና የጸጥታ ምክር ቤት እስከ ሰኔ 30 ድረስ ለሲቪል አመራር ስልጣን እንዲያስተላልፍ ቀነ ገደብ መስጠቱ የሚታወስ ነዉ፡፡

በሌላ በኩል በሃገሪቱ በጥብጥና አላስፈላጊ ጦርነት ለማስነሳት ጥረት ሲያደርጉ በተገኙ ሃይሎች ላይ እርምጃ  እየተወሰደ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን ይህ ደግሞ በተለይ አይ ኤስ የተሰኘዉን አክራሪ ቡድን ራሱን እንዲያደራጅና ሃገሪቷን የጦርነት ቀጠና ለማድረግ ክፍተት እንደሚሰጣቸዉም በማሳሰቢያነት ተጠቅሷል፡፡

የሱዳን ኮሙኒስት ፓርቲ ባወጣው መግለጫ የሉአላዊ ምክር ቤቱን ሊቀመንበርነት ለወታደራዊ ሃይሉ ለመስጠት በሚደረገዉ ማንኛዉም ስምምነት እንደማይስማማ ነው ያስታወቀው፡፡

ፓርቲዎቹ ባወጡት የጋራ መግለጫ በሁለቱም አካላት በኩል ያለዉ የጋራ ኮሚሽኖች ከስምምነት  ለመድረስ ጥረቱን አጠናክሮ ይቀጥላል ነው ያሉት፡፡ (ምንጭ፡-ሱዳን ትሪቡን)