ኦማር ሀሰን አልበሽር በሙስና ወንጀል ክስ ተመሰረተባቸው

የቀድሞው የሱዳን ፕሬዚዳንት ኦማር ሀሰን አልበሽር በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ክስ ተመሰረተባቸው፡፡

ኦማር ሀሰን አልበሽር ክስ የተመሰረተባቸው በህገ ወጥ መንገድ ሀብት በማካበት እና በስልጣን ዘመናቸው ባወጁት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መሆኑን የሀገሪቱ አቃቤ ህግ አስታውቋል፡፡

በመፈንቅለ መንግስት ባገኙት ስልጣን ለ30 ዓመታት መንበረ ስልጣኑን ተቆጣጥረው የቆዩት ኦማር ሀሰን አልበሽር፥ ለወራቶች በሀገሪቱ በተካሄደው ህዝባዊ ተቃውሞ ምክንያት ከስልጣን መውረዳቸው የሚታወስ ነው፡፡

ኦማር ሀሰን ከስልጣን መውረዳቸውን ተከትሎም የወታደራዊ የሽግግር ምክር ቤቱ ሀገሪቱን እያስተዳደረ ይገኛል መረጃዉ ያገኘነዉ ከቢቢሲ ነዉ።

ምክር ቤቱ ለህዝባዊ አስተዳደር ስልጣኑን እንዲያስረክብ ከፍተኛ ግፊት እየተካሄደበት መሆኑ ይታወቃል ፡፡