የሱዳን የተቃውሞ መሪዎች ከኢትዮጵያና ከአፍሪካ ህብረት አዲስ የሽግግር እቅድ መቀበላቸውን ገለጹ

ሱዳን ውስጥ የወታደራዊ አስተዳደሩ ስልጣኑን ለሲቪሉ እንዲያስረክብ ግፊት በማድረግ ላይ ያሉ የተቃውሞ መሪዎች በኢትዮጵያና በአፍሪካ ህብረት የተዘጋጀ አዲስ የሽግግር እቅድ መቀበላቸውን ተናግረዋል።

በአዲሱ እቅድ በሽግግር የህግ አውጭ ምክር ቤቱ ውስጥ ብዙሃን የሲቪል ተወካዮች እንዲኖሩ መታሰቡ ተጠቁሟል።

ሆኖም የሽግግር ምክር ቤቱ ውክልና በአሃዝ ዝርዝር ምን መምሰል እንዳለበት የሚያሳይ ዝርዝር መረጃ ስለመያዙ የተባለ ነገር የለም።

“ለነፃነትና ለለውጥ ጥምረት” የተሰኘው የተቃውሞ ሃይሎች ስብስብ ባወጣው መግለጫ አዲሱ የሽግግር እቅድ ለውሳኔ እንደሚያበቃ ጠቁመዋል።

የሱዳን ወታደራዊ ሽግግር ምክር ቤት ኢትዮጵያና የአፍሪካ ህብረት የሀገሪቱን ፖለቲካዊ ሽግግር ለማሳካት በትብብር ጥረት እንዲያደርጉ መጠየቁ ይታወሳል መረጃዉ የአል ጄዚራ ነዉ።