የሱዳን ወታደራዊ ምክር ቤት እና ተቀዋሚ ሀይሎች ስልጣን ለመጋራት ከሚያስችል ስምምነት ላይ ደረሱ

የሱዳን ወታደራዊ የሽግግር ምክር ቤትና ተቃዋሚዎች ስልጣን ለመጋራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡

ስምምነቱን ተከተሎ የሱዳን ወታደራዊ ምክር ቤት ምክትል ሊቀመንበር መሀመድ ሃምዳን ዶጋሊ ባደረጉት ንግግር የፓለቲካ ስምምነቱ ለሀገሪቱ ታሪካዊ ክስተት ነው ብለዋል፡፡

በተጨማሪም ሕገ-መንግሥቱን በተመለከተ በመጪው አርብ ከስምምነት ደርሰው እንደሚፈራረሙ ይጠበቃል።

ሁለቱ የሱዳን የፓለቲካ ሀይሎች በኢትዮጵያና የአፍሪካ ህብረት በቀረበው ረቀቅ የሽግግር እቅድ በቅርቡ ስምምነት ላይ መድረሳቸው የሚታወስ ነው፡፡/ሱዳን ትሪቡን/