በናይጀሪያ ስድስት የእርዳታ ሰራተኞች መሰወራቸው ተነገረ

በናይጀሪያ ስድስት እርዳታ ሰራተኞች የተሰወሩት የሰብዓዊ እርዳታ ግብዓት የጫኑ ተሸክርካሪዎች ላይ በታጣቂዎች ጥቃት ከተፈጸመ በኋላ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በጥቃቱ አንድ አሽከርካሪ ወዲያውኑ ህይወቱ ሲያልፍ ሁለት አሽከርካሪዎች፣ ሁለት የጤና ባለሙያዎች እና ሌሎች የእርዳታ ሰራተኞች መሰወራቸው ተነግሯል፡፡

ተሽከርካሪዎቹ እርዳታ ጭነው ዳማሳክ ወደ ተባለው የሀገሪቱ አካባቢ ሲጓዙ በታጠቁ ሀይሎች ጥቃቱ እንደተፈጸመቸው የናይጀሪያ የአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ ዳይሬክተር ሻሽዋት ሳራህ ተናግረዋል፡፡

ቦኮሃራም ላለፉት አስርት አመታት በአካባቢው ከሚፈጽማቸው ጥቃቶች ጋር በተያያዘ በርካታ ሰዎች ለችግር መጋለጣቸውንም ዳይሬክተሩ ገልጸዋል፡፡

በናይጀሪያ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ እርዳታ አስተባባሪ የሆኑት ኢድዋርድ ካሎን በበኩላቸው የቀጠናው የደህነት ስጋት ቀጣይነት ያለው መሆኑን ተናግረዋል፡፡

(ምንጭ፦ አልጀዚራ)