በሞቃዲሾ የሚገኘው የቱርክ ወታደራዊ ካምፕ 152 የሶማሊያ ወታደሮችን አሰለጠነ

በሶማሊያ ሞቃዲሾ የሚገኘው የቱርክ ወታደራዊ ካምፕ 152 የሶማሊያ ወታደሮች ማሰልጠኑን አስታወቀ፡፡

በቱርክ አጋዥነት በሶማሊያ የሚደረገው ወታደራዊ ስልጠና ሀገሪቱን ከሚያምሳት የሽብርተኝነት አደጋ ለመታደግ መሆኑንም ቱርክ ገልፃለች፡፡

ቱርክ በአፍሪካ ከከፈተቻቸው ወታደራዊ ካምፖች መካከል በ2017 እ.አ.አ በሞካዲሾ የከፈተችው ይጠቀሳል፡፡

ይህ ካምፕ ከ1 ሺህ 500 በላይ የሶማሊያ ወታደሮችን አሰልጥኖ ወደ ስራ ማሰማራቱን የቱርክ መከላከያ ሚኒስቴር ሁሉሲ አካር አስታውቀዋል፡፡

ቱርክ በሶማሊያ አሰልጥና ካስመረቀቻቸው ወታደሮች መካከልም 81 የሚደርሱት በመቶ አለቃ ማዕረግና ከ71 በላይ የሚሆኑት ደግሞ በ50 አለቃ ማዕረግ እንደተመረቁ እና የሰላም ማስከበር ስራቸውን እንደሚሰሩ ነው ሚኒስትሩ ያስታወቁት፡፡

የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሙሀመድ አብዱላሂ ፋርማጆ 152 የሶማሊያ ወታደሮችን በመገኘት ያስመረቁ ሲሆን÷ ቱርክ በሶማሊያ ሽብርተኝነትን ለማጥፋት እያደረገች ስላለው እገዛ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

በሞቃዲሾ ቱርክ ካስመረቀቻቸው ወታደሮች ጎን ወታደራዊ መጠለያዎችን እና ትምህርት ቤቶችን መገንባቷን የዘገበው ሲጂቲኤን ነው፡፡