በግብፅ 130 ታራሚዎች የረሃብ አድማ አደረጉ

አመንስቲ ኢንተርናሽናል እንደገለፀው በግብፅ ዋና ከተማ ካይሮ በሚገኘው ማረምያ ቤት ውስጥ የሚገኙ 130 ታራሚዎች በሰብአዊ መብት አያያዝ ጉድለትና ቤተሰብ እንዳይጠይቃቸው በመደረጉ ከስድስት ሳምንታት በላይ የረሃብ አድማ በማድረግ ተቃውሟቸው አንፀባርቀዋል፡፡ 

ከፍተኛ ጥበቃ በሚደረግለት በደቡባዊ ካይሮ በሚገኘው ማረሚያ ቤት የስራ ሃላፊዎቹ ታራሚዎቹን በመደብደብ እና በኤሌክትሪክ ሾክ እየቀጧቸው እንደሆነ አመንስቲ ኢንተርናሽናል ታራሚዎቹን ዋቢ አድርጎ ገልጿል፡፡

የህግ ታራሚዎቹ ከቤተሰቦቻቸው ጋር እንዳይገናኙ በማድረግ ግልፅ የሆነ ወንጀል እየሰሩ ያሉ የማረምያ ቤቱ የስራ ሃላፊዎች የግብፅ ህዝብና አለም አቀፍ ማህበረሰብ ሊያወግዛቸው እንደሚገባ አመንስቲ ኢንተርናሽናል መግለፁን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡