የሞቃዲሾ ከተማ ከንቲባ በቦንብ ጥቃት ህይወታቸው አለፈ

የሞቃዲሾ ከተማ ከንቲባ አብዱራህማን ዑመር ህይወታቸው ያለፈው በጽህፈት ቤታቸው በተፈፀመ የቦንብ ጥቃት መሆኑ ተገልጿል፡፡

ከንቲባው ከቦንብ ጥቃቱ  በኋላ በኳታር ህክምና ሲደረግላቸው ቆይቶ  ህይወታቸው ማለፉን ነው የሶማሊያ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት የገለፁት፡፡

በብሪታኒያ የተወለዱት ከንቲባው  የሌበር ፓርቲ አባል ሆነው ሲያገለግሉ ከቆዩ በኋላ በጦርነት የስትታመስ የቆየችውን ሶማሊያ  መልሶ በመገንባቱ ሂደት አስተዋፅኦ ለማድረግ በማሰብ ነበር ወደ ሶማሊያ ያቀኑት።

የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሙሃመድ አብዱላሂ የከንቲባውን ህልፈት ተከትሎ በመላ ሀገሪቱ የሶስት ቀናት ብሄራዊ ሃዘን ማወጃቸውን ሲጂቲኤን ዘግቧል፡፡